ደረጃው ክለቦች ባለፉት አራት የውድድር ዘመናት በሊጎች እና በአህጉራዊ ውድድሮች የነበራቸውን አፈጻጸም ከግምት ውስጥ አሰግብቷል
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በአውሮፓ በሚካሄዱ ሊጉች የሚጫወቱ እግር ኳስ ቡድኖችን ደረጃ አውጥቷል፡፡
ማህበሩ በሚያወዳድራቸው ሶስት የውስጥ ውድድሮች እና ቡድኖቹ በሚጫወቱበት ሊግ የነበራቸውን አፈጻጸም በመስፈርተነት ተጠቅሟል፡፡
በዚህም የ2024/25 ክለቦች እስከ 20 ያላቸውን ደረጃ ያወጣ ሲሆን በዚህም የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ 6 ክለቦች ምርጥ 20 ውስጥ ማካተት ችሏል፡፡
ማንችስተር ሲቲ በደረጃው በቀዳሚነት ሲቀመጥ የዘንድሮው የሻምፒውንስ ሊግ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ ተከታዩን ደረጃ በአውሮፓ የእግር ኳስ ማህበር አግኝቷል።
ባየር ሙኒክ ፣ ሊቨርፑልና ሮማ እስከ አምስት ያለውን ደረጃ የያዙ ክለቦች ናቸው።
በእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው አርሰናል 19 ደረጃን የያዘ ሲሆን መጥፎ የውድድር አመትን ያሳለፈው ማንችስተር ዩናይትድ በአንፃሩ 14 ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ተመላክቷል።
የዩሮፓ ሊግ አሸናፊው አታላንታ 20 ኛ ደረጃን የያዘ የወቅቱ ክለብ ነው፡፡
የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የክለቦችን ደረጃ በዚህመልክ የሰጠው በሻምፒውንስ ሊግ ፣ በዩሮፓ ሊግና በኮንፍረንስ ሊግ ባስመዘገቡት ውጤት ነው፡፡
በተጨማሪም ባለፋት አራት ተከታታይ የውድድር ዘመናት ባስመዘገቡት ውጤት ደረጃ ወጥቶላቸዋል።