ከለንደን እስከ ታይላንድ፤ ከሞሱል እስከ ዱባይና ካይሮ ደማቅ የርችት መተኮስ፣ የሙዚቃ ድግሶች እና ልዩ ልዩ የበዓል ድግሶች ተካሂደዋል
የጎርጎሮሳውያንን የዘመን ቀመር የሚከተሉ ሀገራት የ2023 አዲስ አመትን ተቀብለዋል።
የፓስፊኳ ኪሪባቲም አዲሱን አመት በማክበር ቀዳሚዋ ሆናለች።
አውስትራሊያ እና የአሜሪካዋ ሃዋይም አዲሱን አመት ቀደም ብለው ማክበር ከጀመሩት ይጠቀሳሉ።
ከለንደን እስከ ታይላንድ፤ ከሞሱል እስከ ዱባይና ካይሮ ደማቅ የርችት መተኮስ፣ የሙዚቃ ድግሶች እና ልዩ ልዩ የበዓል ድግሶች ተካሂደዋል።
በአዲሱ አመት አቀባበል ወቅት የበርካቶችን ቀልብ ከያዙ ምስሎች የተወሰኑትን እነሆ፦
በዱብይ የአለምችን ሰማይ ጠቀሱ ፎቅ ቡርጀ ከሊፋ ደማቁን የአዲስ አመት አቀባበል አስተናግዷል
በእንግሊዝም የዌስትሚኒስተር ስአት በርችቶች ደምቆ አምሽቷል
በፈረንሳይ የአርበኞች ሃውልት የአዲስ አመት አቀባበል
በታይላንድ መዲና ባንኮክ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አዲሱን አመት ሲቀበሉ
በቻይና እና ሌሎች የእስያ ሀገራት ከሁለት አመት በኋላ ሰዎች ተሰባስበው አዲሱን አመት ተቀብለዋል። ከሁለት አመት በፊት የኮሮና ወረርሽኝ የተነሳባት የውሃን ከተማ ነዋሪዎችም ፊኛዎችን ወደ ሰማይ ፡በመልቀቅ አዲሱን አመት በደስታ ተቀብለዋል።
የጀርመኗ ሙኒክ አዲሱን አመት በርችት ስትቀበል
ከሩስያ ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባች 10 ወራት ያለፋት የወትሮው ድባብ ቢቀዘቅዝም አዲሱን አመት በተስፋ ተቀብላለች
የኢራቋ ጥንታዊ ከተማ 2023ን በርችት ስትቀበል
በአውስትራሊያ የሲድኒን ሰማይና ጀልባዎች ያደመቀው የአዲስ አመት አቀባበል
በብራዚል የሪዮ ደጄኔሮ የባህር ዳርቻ የአዲስ አመት አቀባበል