ውድ እቃዎችን እና ቦምቦችን ጨምሮ ቅንጡ እቃዎች የሚገኝበት ሀይቅ
ባልና ሚስቶቹ በዚሁ ሀይቅ ላይ 100 ሺህ ዶላር ግምት ያላቸው ውድ እቃዎችን አግኝተዋል
ፖሊስ በበኩሉ በሀይቁ ላይ የሚገኙ ንብረቶችን በነጻነት ለግል ጥቅም ማዋል ይቻላል ሲል ፈቃድ ሰጥቷል
ውድ እቃዎችን እና ቦምቦችን ጨምሮ ቅንጡ እቃዎች የሚገኝበት ሀይቅ
የዓለማችን ቁጥር አንድ የዲፕሎማሲ ማዕከል የምትባለው ኒዮርክ በሀይቋ ዙሪያ ሰዎች ውድ ዋጋ ያላቸው ንብረቶችን ሲፈልጉ ማየት እየተለመደ መጥቷል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ከሆነ ብዙ ሰዎች አሳ ለማጥመድ በሚመስል መልኩ ወደ ሀይቁ ሲሁዱ ቢስተዋልም ከባባድ እቃዎችን ማንሳት የሚችሉ ማግኔቶችን ወደ ሀይቁ እየተጣሉ ናቸው፡፡
በዚህ በሀይቁ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት የተጣሉ እና ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የተጣሉ ውድ እቃዎችን ጨምሮ ሌሎች ጠቃሚ እና አውዳሚ ቁሳቁሶች እየተገኙ ነውም ተብሏል፡፡
በማግኔቶቹ ከሚወጡ ቁሳቁሶች መካከል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ውለው የነበሩ አውዳሚ ቦምቦች፣ የታሸጉ ውድ ቁሳቁሶች፣ ወርቅ እና ሌሎችም ንብረቶች ተጠቅሰዋል፡፡
አንድ ባልና ሚስት በዚሁ የኒዮርክ ሀይቅ ውስጥ በላኩት ማግኔት አማካኝነት 100 ሺህ ዶላር ዋጋ ያላቸው ውድ ቁሳቁሶችን ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡
ጀምስ ኬን እና ባርቤ አጎስቲኒ የተሰኙት ጥንዶቹ ከሀይቁ ውስጥ ያገኙትን ንብረት ለፖሊስ ቢያስረክቡም የኒዮርክ ፖሊስ ንብረቱ የሌላ ሰው መሆኑ ባለመመዝገቡ ምክንያት እንዲጠቀሙበት መልሶ ሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡
የኒዮርክ ፖሊስም በተደጋጋሚ ሰዎች ከሀይቁ ውስጥ ብዙ ንብረቶችን እያወጡ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ውድ ዋጋ ያላቸው ናቸው የተወሰኑት ደግሞ በውሃ የተጎዱ ይሆናሉ ሲል አስታውቋል፡፡
ኒዮርክ ከተማ የአይጦችን እርባታ ለመከላከል የወሊድ መከላከያ ልትሰጥ መሆኗን ገለጸች
ከሀይቁ ውስጥ የሚገኙ ንረቶች ባለቤትነታቸው ባለመታወቁ እና ባለመመዝገባቸው ምክንያት ያገኟቸው ሰዎች ንብረቶቹን እንዲወስዱ እያደረግን ነውም ብሏል፡፡
ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ሀይቅ ለይ ማግኔት መላክ እንደጀመሩ የሚናገሩት እነዚህ ጥንዶች የጦር መሳሪያ፣ ቦምብ እና የተሟላ ሞተር ሳይክል ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
እነዚህ ንብረቶች መቼ፣ ለምን እና በማን ወደ ሀይቁ እንደገቡ እስካሁን በቂ መረጃ እንዳልተገኘ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡