ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በርካቶች ቆስለው ስጦታውንም ሳይወስዱ መመለሳቸው ተነግሯል
የኒውዮርክ ዩኒየን አደባባይ ትናንት በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ተጥለቅልቋል።
በቀጥታ የዩቲዩብ ስርጭት የሚታወቀው ካይ ሴናት የላፕቶፕ ኮምፒውተር እና ጌም መጫወቻዎችን በቦታው በነጻ እንደሚሰጥ መግለጹ ነው የትርምሱ ምክንያት።
የነጻ ስጦታውን ለመውሰድ የጓጉ በርካቶች ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውና በትርምሱ ተረጋግጠው መጎዳታቸው ተገልጿል።
የ21 አመቱ ሴናት ትዊች በተባለው የቪዲዮ ጨዋታዎች ማሰራጫ መተግበሪያ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን፤ በዩቲዩብ ደግሞ 4 ሚሊየን ተከታዮች አሉት ተብሏል።
የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic