ኒውዚላንድ መጪውን ትውልድ ሲጋራ ከማጨስ የሚታደግ ሕግ አጸደቀች
ሕጉ በአሁኑ ትውልድ ተወዳጅ እየሆነ የመጣው የኤሌክትሮኒክ ሲጋራን አይመለከትም ተብሏል
በአዲሱ ሕግ መሰረት ከጥር 1 ቀን 2009 ወዲህ የተወለዱት የሀገሪቱ ዜጎች የትምባሆ ምርቶች መግዛት አይችሉም
ኒውኒውዚላንድ መጪውን ትውልድ ሲጋራ ከማጨስ የሚታደግ ሕግ አጸደቀች።
ኒውዚላንድ ከመጪው አመት ጀምሮ ማንኛውም ሰው የትምባሆ ምርቶችን እንዳይጠቀም የሚያግድ ህግ አጸደቀች፡፡
የሀገሪቱ ፓርላማ ባጸደቀው ሕግ መሰረት ከፈረንጆቹ ከጥር 1 ቀን 2009 ወዲህ የተወለዱት የሀገሪቱ ዜጎች የትምባሆ ምርቶች መግዛት አይችሉም ተብሏል፡፡
በቀጣይ ትምባሆ መግዛት የሚችሉ ሰዎች ቁጥር ሕጉን እያሻሻሉ የመቀነሱ ስራ እንደሚሰራም የዘ-ጋርዲያን ዘገባ ያመለክታል፡፡
ለምሳሌ በፈረንጆቹ 2050 ሲጃራ ማጤስ የሚፈቅድላቸው ሰዎች እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ የሆነ ብቻ ይሆናሉም ነው የተባለው፡፡
አዲሱን ሕግ ለሀገሪቱ ፓርላማ ያቀረቡት የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር አየሻ ቨራል፡ ይህ እርምጃ " ከትንባሆ ነጻ ወደ ሆነው ትውልድ " የሚወስደን ነው ብለዋል፡፡
"በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ረጅምና ጤናማ ህይወት የሚኖሩ ይሆናል፤ የጤናው ሴክተርም በትንባሆ የሚመጡ በሽታዎችን ለማከም ሲያወጣ የነበረውን 3.2 ቢልዮን ዶላር ወጪ ያስቀራል " ሲሉም ተናግረዋል ዶክተር ቨራል፡፡
በኒውዚላንድ ያለው ሲጋራን የማጤስ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡
በወርሃ ህዳር ይፋ የተደረጉ አሃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በአዋቂዎች የእድሜ ክልል ከሚገኙት በየቀኑ ሲጋራ የሚያጨሱት 8 በመቶ ብቻ ናቸው፡፡ ይህም ባለፈው አመት ከነበረው የ9.8 በመቶ የሲጋራ ተጠቃሚዎች መጠን መጠነኛ ለውጥ ያሳያል ተብሏል፡፡
የአሁኑ አዲስ ሕግ ከተጠቃሚዎች በዘለለ በትንባሆ ሻጭ ኩባኒያዎች ላይም ገደብ የሚጥል ነው ተብሏል፡፡
ቢዘህም በመላ ሀገሪቱ ያሉትትን 6ሺህ የትንባሆ ምርት የሚያቀርቡ ኩባኒያዎች ወደ 600 ለማውረድና በትንባሆ ምርቶች ላይ የሚገኘውን የኒኮቲን መጠን ለመቀነስ እቅድ ተይዞ እንደሚሰራ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ቨራል ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ቨራል"ኒኮቲን ሱስ ወደማይሆንበት ደረጃ የሚወርድ ይሆናል"ም ብለዋል፡፡
ይሁን እንጅ አዲሱ ሕግ ከሲጃራ በዘለለ በአሁኑ ትውልድ ተወዳጅ እየሆነ የመጣው የ'ቬፕ' (ኤሌክትሮኒክ ሲጋራ)ን እንደማይመለከት ተገልጿል፡፡