በሱዳን በከባድ ዝናብ ምክንያት የ73 ሰዎች ህይወት አለፈ
ባለፈው ሳምንት ተመድ በጎርፉ የተጎዱትን ለመርዳት 1.6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልጾ ነበር
ዝናቡ ከሰው ህይወት መጥፋት በሻገር 17ሺ ቤቶች ሙሉበሙሉ እንዲወድሙ አድርጓል
ዝናቡ ከሰው ህይወት መጥፋት በሻገር 17ሺ ቤቶች ሙሉበሙሉ እንዲወድሙ አድርጓል
የሱዳን የህዝብ ጥበቃ ብሄራዊ ምክርቤት እንዳስታወቀው በሱዳን በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በጠቅላላ የ73 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቋል፡፡
በሱዳን የዝናብ ወቅት ከገባበት ጀምሮ በሁሉም የሱዳን ግዛቶች 73 መሞታቸውንና 29 ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ምክርቤቱ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡ በዝናቡ ምክንያት 17ሺ ቤቶች ሙሉበሙሉ መውደማቸውንና ወደ 26ሺ የሚጠጉ የቀንድ ከብቶች ተገድለዋል፡፡
ሱዳን ከሰኔ እስከ ጥቅምት ባለው ጊዜ በሚጥለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የጎርፍ አደጋ ይደርስባታል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሱዳን የመስኖና የውሃ ሀብት ሚኒስቴር የጎርፍ ኮሚቴ የሚመለከታቸው አካላትና ህዝቡ አደጋውን ነቅተው እንዲከታተሉና ህይወትና ንብረት ለመከላከል የሚያስችል መላ መዘየድ እንዳለባቸው ማሳሰበቢያ አስተላልፏል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ቃል አቀባይ ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቁት በሱዳን ከሚገኙት 18 ግዛቶች ውስጥ በ17ቱ እየተከሰተ ባለው ከባድ ዝናብና ጎርፍ ምክንያት ወደ 220ሺ የሚጠጉ ሰዎች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል፡፡
“ከ20ሺ በላይ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ተጨማሪ 20ሺ ቤቶችም” እንዲሁ በጎርፍ ምክንያት መውደማቸውን የገለጹት የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ የሆኑት ስቴፋኒ ዱጃሪክ ገልጸው ነበር፡፡
ቃል አቀባዩ ተመድ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን 1.6 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መጠየቁን መግለጻቸውም ይታወሳል፡፡