ከተማዋ በወቅቱ ይህን ህግ ያወጣችው የትዳር ፍቺን ለመከላከል በሚል እንደነበር ተገልጿል
ኒውዮርክ ከተማ ዝሙትን ከወንጀልነት ሰረዘች።
የዓለማን ቁጥር አንድ የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው ኒውዮርክ ከተማ ዝሙት መፈጸም የሚከለክለውን ህግ ሰርዛለች።
ከተማዋ በ1907 ዝሙት መፈጸምን የሚከለክል ህግ ያወጣች ሲሆን ይህን ህግ ተላልፎ የተገኘ ሰው የሶስት ወር እስር ያስቀጣም ነበር።
ይሁንና ከተማዋ ይህን የዝሙት ህግ ከወንጀልነት የሰረዘች ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ህጉ ወቅቱን አይመጥንም በሚል ነው።
የኒውዮርክ ከንቲባ ካቲ ሆቹል ህጉን በይፋ ሶስት ወር ቅጣትን የሚጥለውን ህግ መሰረዙን ተናግረዋል ።
ከንቲባው አክለውም ህጉ ወቅቱን ያልጠበቀ እና ያረጀ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ከትዳር ውጪ የሚደረግ ወሲብን ለመከልከል በሚል የተዘጋጀው ይህ ህግ አጥፊዎችን ለመያዝ አስቸጋሪ ነው መባሉ ለህጉ መሻር ሌላኛው ምክንያት እንደሆነም ተገልጿል።
ህጉ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ12 ሰዎች ላይ የዝሙት ወንጀል ክስ የተመሰረተ ሲሆን አምስት ሰዎች ብቻ ተቀጥተዋልም ተብሏል።
ለመጨረሻ ጊዜም በዚህ ወንጀል ክስ የተመሰረተው በ2010 ዓመት ላይ ሲሆን ክሱ በስምምነት ተቋርጧል።
ኒዮርክ ይህን አነጋጋሪ ህግ በ1960 ላይ ለመሰረዝ አስባ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ የህጉ መሰረዝ የትዳር ፍቺን ያባብሳል በሚል ፖለቲከኞች ባሰሙት ተቃውሞ ምክንያት ሳይሰረዝ ቀርቷል።