ኔታንያሁ ተደራዳሪ ቡድን ወደ ግብጽ እና ኳታር ለመላክ ተስማሙ
ግብጽ እና ኳታር ተፋላሚዎቹ እስራኤል እና ሀማስ የታጋቾችን መለቀቅ የሚያካትት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው
እስራኤልም ሆነች ሀማስ ተኩስ ለማቆም ፍቃደኛ ቢሆኑም ያቀረቧቸው ቅደመ ሁኔታዎች ግን አንዱ የሌላኛውን እየተቃወመ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም
ኔታንያሁ ተደራዳሪ ቡድን ወደ ግብጽ እና ኳታር ለመላክ ተስማሙ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ጉዳይ የሚደራደር ቡድን ወደ ግብጹ እና ኳታር ለመላክ በትናንትናው እለት መስማማታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አስታውቋል።
ግብጽ እና ኳታር ተፋላሚዎቹ እስራኤል እና ሀማስ የታጋቾችን መለቀቅ የሚያካትት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።
- ኔታንያሁ እስራኤል እየጨመረ ለመጣው አለማቀፍ ጫና ሸብረክ እንደማትል ተናገሩ
- ኔታንያሁ የእስራኤልን የልኡካን ቡድን የዋሽንግተን ጉዞ እቅድ መሰረዛቸው አሜሪካን አስቆጣ
ጽ/ቤቱ እንደገለጸው ኔታንያሁ ከእስራኤል የስለላ ድርጅቶች ኃላፊዎች እና ከሞሳድ ጋር ተነጋግረው እስራኤልን የሚወክል ቡድን ለድርድሩ ወደ ዶሃ እና ካይሮ እንዲሄድ አጽድቀዋል።
እስራኤልም ሆነች ሀማስ ተኩስ ለማቆም ፍቃደኛ ቢሆኑም ያቀረቧቸው ቅደመ ሁኔታዎች ግን አንዱ የሌላኛውን እየተቃወመ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም።
ሀማስ እሰራኤል ከጋዛ ሙሉ በሙሉ ለቃ እንድትወጣ እና ያሰረቻቸውን ፍልስጤማውያን እንድትለቅ ይፈልጋል። እሰራኤል በአንጻሩ ሀማስን ጨርሳ መደምምሰ እና የጋዛን የደህንነት ሁኔታ የምትቆጣጠርበት ወይም በፈለገችበት ጊዜ እንድትገባ የሚያደረግ ሁኔታ እንዲፈጠር ትፈልጋለች።
ከዚህ በተጨማሪም እስራኤል የፍልስጤም ሀገር አንዲቋቋም አትፈቅድም።
የአረብ ሀገራት እና አሜሪካ እስራኤል የፍልስጤምን ሀገርነት መፍቀድ አለባት፣ ካልፈቀደች ዘላቂ ሰላም አይመጣም የሚል አቋም ሲያንጸባርቁ ይደመጣሉ።
እስራኤል ከሀማስ ጋር በምታደርገው ጦርነት ቀዳሚ ደጋፊ የሆነችው አሜሪካ የአቋም ለውጥ የማድረግ ዝንባሌ እየታየባት ነዉ።
በቅርቡ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የቀረበው የተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብ የእስራኤል ዋና አጋር የሆነችው አሜሪካ ጽምጸ ተአቅቦ በማድረጓ ጸድቋል።
በዚህ የተቆጣችው እስራኤል ወደ ዋሽንግተን ሊደረግ የነበረን የከፍተኛ ባለስልጣናት የጉዞ እቅድ መሰረዟም ይታወሳል።