የንጹሃንን ጉዳት ለመቀነስ ያደረግነው ጥረት "ስኬታማ አልሆነም"- ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ
በጋዛ ጦርነት እያካሄዱ ያሉት የእስራኤል ወታደሮች በአል ሽፋ ሆስፒታል ውስጥ ሀማስ ይጠቀምበት የነበረ ክፍል ማግኘታቸውን ገልጸዋል
ነገረግን ሀማስ በመግለጫው ቡድኑ አልሽፋ ሆስፒታልን ለወታደራዊ አላማ ተጠቅሞበታል የሚለው "የሀስት ትርክት" ነው ብሏል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኔያሁ በጋዛ በሚደረገው ጦርነት የንጹሃንን ጉዳት ለመቀነስ ያደረጉት ጥረት ስኬታማ አለመሆኑን ተናግረዋል።
በጋዛ ጦርነት እያካሄዱ ያሉት የእስራኤል ወታደሮች በአል ሽፋ ሆስፒታል ውስጥ ሀማስ ይጠቀምበት የነበረ ያሉትን ክፍል ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ጦሩ በሆስፒታሉ ስር ወደሚገኝ ዋሻ ያስገባል ያለውን መግቢያመሰ በቪዲዮ አሳይቷል። ከዚህ በተጨማረም ጦሩ በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ብዙ መሳሪያ የተጫነበት መኪና አግኝታለሁ ብሏል።
ነገረግን ሀማስ በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ ቡድኑ አልሽፋ ሆስፒታልን ለወታደራዊ አላማ ተጠቅሞበታል የሚለው "የሀስት ትርክት" ነው ብሏል።
ባለፈው ጥቅምት ወር ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ 1200 እስራኤላውያንን መግደሉን ተከትሎ እስራኤል መጠነሰፊ የሆነ የአጸፋ ምላሽ እየሰጠች ትገኛለች።
የጋዛ የጤና ባለስልጣናት እንደሚናገሩት በእስራኤል ጥቃት እስካሁን ከ11ሺ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔናንያሁ ከአሜሪካው ቴሌቪዥን ሲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እስራአል የንጹሃንን ጉዳት ለመቀነስ ያደረገችው ጥረት አለመሳካቱን ገልጸዋል።
"የትኛውም የንጹሃን ግድያ ዘግናኝ ነው። ንጹሃንን እንዳይጎዱ ጥንቃቄ አድርገን ነበር። ነገርግን ሀማስ ለአደጋ እንዲጋለጡ አደረጋቸው።"
ኔታንያሁ ንጹሃን እንዳይጎዱ"በራሪ ወረቀት በትነናል፤ በእጅ ስልካቸው ደውለናል፤ በዚህም ብዙዎች ሸሽተዋል" ብለዋል።