ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የፍልስጤምን ሀገር መሆን እንደሚቃወሙ ተናገሩ
ኃይትሀውስ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን ዘመቻ የምትቀንስበት ጊዜ አሁን ነው ሲልም አስታውቆ ነበር
ኔታንያሁ ከአሜሪካ ተቃውሟቸውን የገለጹት አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል ለፍስጤም ነጻነት በር የማትከፍት ከሆነ "አስተማማኝ ደህንነት" አይኖራትም ካሉ ከአንድ ቀን በኋላ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከጦርነቱ በኋላ የፍልስጤምን ሀገር መሆን እንደሚቃወሙ ተናገሩ።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ያለው ጦርነት ካበቃ በኋላ የፍስጤም ሀገር መሆንን እንደሚቃወሙ ለአሜሪካ መናገራቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናው እለት እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ እንድትቀንስ እና ከጦርነት በኋላ ለሚኖረው የፍልስጤም መንግስት ምስረታ እርምጃ እንድትወስድ የሚጠይቀውን የአሜሪካ ጥሪ ውድቅ አድርጋዋለች።
ይህ ሁለቱ አጋሮች የጋዛ ጦርነት በሚኖረው አድማስ እና ከጦርነት በኋላ በሚኖረው ሁኔታ ላይ ልዩነት እንዳላቸው የሚያሳይ ነው።
"እኛ ይህን በተለየ መልኩ ነው የምናየው"ሲሉ የኋይትሀውስ የብሄራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ክርቢይ ተናግረዋል።
ኔታንያሁ ለአሜሪካ ተቃውሟቸውን የገለጹት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል ለፍስጤም ነጻነት በር የማትከፍት ከሆነ "አስተማማኝ ደህንነት" አይኖራትም ካሉ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
ኃይትሀውስ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን ዘመቻ የምትቀንስበት ጊዜ አሁን ነው ሲልም አስታውቆ ነበር።
ኔታንያሁ በቴሌቪዥን በተላለፈ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ቀርበው እስራኤል የሀማስ ታጣቂዎችን ሳታጠፋ እና ሁሉንም ታጋቾች ሳታስለቅቅ ጥቃቷን እንደማታቆም ተናግረዋል።
እነዚህ ግቦች አያሳኩም የሚሉ ትችቶችን ውድቅ ያደረጉት ኔታንያሁ ጥቃቱን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዝተዋል።
ባለፈው አመት ጥቅምት ወር ሀማስ ያልተጠበቀ የሚባል ጥቃት በእስራኤል ማድረሱን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰለማዊ ሰዎች ተገድለዋል፣ ቀጣናዊ ውጥረትም እንዲነሳ ምኬንያት ሆኗል።