የኒካራጓዋ ቆንጆ 'የሚስ ዩኒቨርስ 2023' አሸናፊ ሆነች
ለ72ኛ ጊዜ የተካሄደውን ይህን ውድድር በርካታ ታዋቂ ሰዎች ዳኝነት በመስጠት ተሳትፈዋል

ከ84 ሀገራት የተውጣጡ ቆንጆ ሴቶች በተሳተፉበት በዚህ ውድድር የታይላንዷ ወጣት ሴት አኔቶኒያ ፖርሲልድ ሁለተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች
የኒካራጓዋ ቆንጆ 'የሚስ ዩኒቨርስ 2023' አሸናፊ ሆነች
የደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ኒካራጓ ቆንጆ ሸኒዝ ፖላሲዮስ በሳልቫዶራን ዋና ከተማ ሳንሰልቫዶር በተካሄደው የውድድሩ ማጠቃለያ ላይ 'የሚስ ዩኒቨርስ 2023'ን ዘውድ ደፍታለች።
ከ84 ሀገራት የተውጣጡ ቆንጆ ሴቶች በተሳተፉበት በዚህ ውድድር የታይላንዷ ወጣት ሴት አኔቶኒያ ፖርሲልድ ሁለተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።
ለ72ኛ ጊዜ የተካሄደውን ይህን ውድድር በርካታ ታዋቂ ሰዎች ዳኝነት በመስጠት ተሳትፈዋል።
ሱፐርሞዴል ሀሊማ አደን፣ ካርሰን ክሬስሊይ፣ የቲክቶክ ተጽእኖ ፈጣሪዋ አቫኒ ግሬጅ፣ ሁለት የቀድሞ ሚስ ዩኒቨርስ አሸናፊዎች በዳኝነት ቡድኑ ውስጥ ከተካተቱ መካከል ይገኙበታል።
'ሚስ ዩኒቨርስ' በአሜሪካ እና መቀመጫውን ታይላንድ ባደረገው ሚስ ዩኒቨርስ ኦርጋናይዜሽን አማካኝነት በየአመቱ የሚካሄድ አለምአቀፍ የቁንጅና ውድድር ነው።
aXA6IDE4LjIwNS4yNi4zOSA=
ejasoft island