ዜጎቻቸው ቆን የሆኑ የ50 ሀገራት ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተቀምጣለች
የዓለማችን 50 የቆንጆዎች ሀገር ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መረጃን በመጠቀም ይፋ የሆነው የዓለማችን የውበት ደረጃ ሕንድን በቀዳሚነት አስቀምጧል።
አማላይነት፣ ውብ፣ ለአይን ማራኪነት እና አካላዊ ቁንጅናን በዋነኛ መስፈርትነት እንደተጠቀሙ ሜይል ኦንላየን ዘግቧል።
ይህ ቴክኖሎጂ የሁለቱንም ጾታዎች ለውበት ማወዳደሪያነት የተጠቀመ ሲሆን ደረጃውን ለማውጣትም አማካይ ነጥብ ወጥቶላቸዋል ተብሏል።
በዚህ መስፈርት መሰረትም ሕንድን በዓለማችን የውበት ደረጃ በአንደኝነት ሲያስቀምጥ አሜሪካን በሁለተኝነት ፣ ስዊድንን በሶስተኝነት አስቀምጧል።
እንዲሁም ጃፓንን አራተኛ፣ ካናዳን አምስተኛ፣ ብራዚል ስድስተኛ፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ዩክሬን እና ዴንሜርክ እስከ 10ኛ ድረስ ያሉትን ደረጃዎች እንደያዙ ተገልጿል።
ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነችው ኢትዮጵያ በቁንና ከዓለም በ32ኛ ደረጃ ላይ ሲያስቀምጥ ሌላኛዋ አፍሪካዊ ሀገር ግብጽን ደግሞ በ44ኛ ደረጃ ላይ ማስቀመጡን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
ጾታዎችን ነጣጥሎ በተሰጠው ደረጃ መሰረትም በሴቶች ውበት ሕንድ፣ ጃፓን እና ስዊድን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያሉ ደረጃዎችን ይዘዋል።
በወንዶች አማላይነት ደግሞ የብሪታንያ ወንዶችን በቀዳሚነት ሲያስቀምጥ ሕንድ በሁለተኝነት እንዲሁም ጣልያንን በሶስተኝነት አስቀምጧል።