ናይጄሪያ እና ኮትዲቯር ለዋንጫ ፍልሚያ ለመድረስ ያደረጉት ጉዞ ምን ይመስል ነበር?
ናይጄሪያ እና ኮትዲቯር ከኢኳቶሪያል ጊኒ እና ከጊኒ ጋር በምድብ አንድ ነበር የተደለደሉት
በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ፣ ኮትዲቫር እና ናይጀሪያ ዋንጫውን ለማንሳት ይፋለማሉ
ናይጄሪያ እና ኮትዲቯር ለዋንጫ ፍልሚያ ለመድረስ ያደረጉት ጉዞ ምን ይመስል ነበር?
በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ፣ ኮትዲቫር እና ናይጀሪያ ዋንጫውን ለማንሳት ይፋለማሉ።
በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ 3ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች
ጨዋታው ዛሬ ምሽት አምስት ሰአት በትልቁ አላሳን ኦታራ ስቴዲየም ይደረጋል።
ሁለቱ ሀገራት ወደ መጨረሻ 16 ቡድኖች ውስጥ ተካተው በጥሎ ማለፍ፣ በሩብ ፍጻሜ በግማሽ ፍጻሜ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ለመጨረሻው ፍልሚያ ደርሰዋል።
ናይጄሪያ እና ኮትዲቯር ከኢኳቶሪያል ጊኒ እና ከጊኒ ጋር በምድብ አንድ ነበር የተደለደሉት።
ከምድቡ ናይጀሪያ በ7 ነጥብ ከኢኳቶሪያሌ ጊኒ ቀጥሏ በሁለተኛ ደረጃ እና ኮትዲቯር ደግሞ በምርጥ 3ኛ ደረጃ ወደ መጨረሻዎቹ 16ቱ ቡድኖች ውስጥ መካተት ችለዋል።
በምድብ ጨዋታ አፈጻጸም ደስተኛ ያልነበረችው ኮትዲቯር አሰልጣኟን ባሰናበተችበት እለት ነበር ወደ 16ቱ ውስጥ ማለፍ የቻለችው።
በምድብ ስድስት ጨዋታ ሞርኮ ዛምቢያን 1-0 በማሸነፏ ነበር አስተናጋጇ ኮትዲቫር ምርጥ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አራተኛ የሆነችው።
ናይጄሪያ በጥሎ ማለፍ ካሜሩንን 2-0፣ በሩብ ፍጻሜ አንጎላን 1-0፣ በግማሽ ፍጻሜ ደቡብ አፍሪካን በመለያ ምት 4-2 በማሸነፍ እና ኮትዲቯር ደግሞ በጥሎ ማለፍ ሴኔጋልን በመለያ ምት 4-5፣ በሩብ ፍጻሜ ማሊን 2-1፣ ግማሽ ፍጻሜ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን 1-0 በግማሽ ፍጻሜ በማሸነፍ ለዋንጫ ጨዋታ ደርሰዋል።
ትናንት ምሽት ደቡብ አፍሪካ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያደረጉትን የደረጃ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ አሸንፋ 3ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።
የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ያልተጠበቁ ውጤቶችን አስተናግዷል።
ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት የሞሮኮ፣ የግብጽ፣ የአልጀሪያ፣ የሴኔጋል እና የጋና ቡድኖች አልተሳካላቸውም።