በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ 3ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች
በሩብ ፍጻሜ ጨዋታው ደቡብ አፍሪካ ኬፕቨርዴን እና ዲአር.ኮንጎ ደግሞ ጊኒን በማሸነፍ ነበር ወደ ግማሽ ፍጻም ማለፍ የቻሉት
ደቡብ አፍሪካ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን በመለያ ምት 6-5 በማሸነፍ 3ኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች
በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ 3ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች።
በኮትዲቯር አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን (ዲአር.ኮንጎን) በመለያ ምት 6-5 በማሸነፍ 3ኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።
ትናንት ምሽት አምስት ሰአት በፍሌክሲ ሆፕሆት ቦይጊ ስቴዲየም የተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ወደ መለያ ምት ያመራው መደበኛው የጨዋታ ጊዜ ያለግብ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው።
የደቡብ አፍሪካው አማካኝ ተጨዋች ተቦሆ ሞኮይና የመጀመሪያዋን ምት ቢስትም ቀጣይ ተከታታይ ስምንተ ምቶች ወደ ግብነት ተቀይረዋል።
ጨዋታውን ለማሸነፍ የዲአር.ኮንጎው አምበል ቻንሴል ምምባ ግብ ማስቆጠር ነበረበት።
ነገርግን የደቡብ አፍሪካው ግብ ጠባቂ ሮንዌን ዊሊያምስ የምምባን ምት በማክሸፉ ምክንያት ሁኔታው ሊቀየር ችሏል።
ዊሊያምስ መስቻክ ኢላ የመታትን ኳስ በድጋሚ ማዳን በመቻሉ ደቡብ አፍሪካ አሸንፋለች።
በጨዋታ ዲአር.ኮንጎ ግብ ማስቆጠር ባትችልም፣ ብልጫ አሳይታ ነበር ተብሏል።
በሩብ ፍጻሜ ጨዋታው ደቡብ አፍሪካ ኬፕቨርዴን እና ዲአር.ኮንጎ ደግሞ ጊኒን በማሸነፍ ነበር ወደ ግማሽ ፍጻም ማለፍ የቻሉት።
የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ያልተጠበቁ ውጤቶችን አስተናግዷል። ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት የሞሮኮ፣ የግብጽ፣ የአልጀሪያ እና የጋና ቡድኖች አልተሳካላቸውም።