ምርጫው በአንዳንድ አካባቢዎች በችግሮች ለእሁድ ቢተላለፍም ሂደቱ ከተጠበቀው በላይ ሰላማዊ ነበር ተብሏል
የናይጄሪያ ምርጫ ኮሚሽን በግዛቶች ውጤቶችን ይፋ ማድረግ ጀመረ።
የምርጫ ጥሰቶች በቅሬታ የቀረቡበት የናይጄሪያ ምርጫ በሳምንቱ መገባደጃ የተካሄደው ሀገራዊ የምርጫ ውጤት ማሳወቅ ተጀምሯል።
ምንም እንኳን ፕሬዝደንት ሙሃማድ ቡሃሪን ለመተካት በሚደረገው ፉክክር አሸናፊ ነኝ ባይ በአጭር ቀናት ይታወቃል ተብሎ ባይጠበቅም፤ የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን በክልሎች ውጤት እያሳወቀ ነው።
ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ወታደራዊ አገዛዝ ካበቃ በኋላ በሁለት ፓርቲዎች የበላይነት የተያዘው የናይጄሪያ ምርጫ በወጣት መራጮች ዘንድ ለአናሳ ፓርቲ እጩ የተሰጠ ድጋፍ ያልተለመደ ጠንካራ ፈተና እንዲኖር አድርጓል።
ይህም በናይጄሪያ የምርጫ ታሪክ የመጀመሪያ ነው ተብሏል።
ቆጠራው በዋና ከተማይቱ አቡጃ ወደ ሚገኘው የምርጫ ኮሚሽኑ የቆጠራ ማዕከል ከመተላለፉ በፊት የፕሬዝዳንታዊ እና የፓርላማ ምርጫ ከእያንዳንዱ የናይጄሪያ 36 ግዛቶች ድምጽ ይሰበሰባል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ሦስቱም እጩ ተወዳዳሪዎች የምርጫ ጉድለት እንደተከሰተ ቅሬታ አቅርበዋል።
በርካታ የምርጫ ጣቢያዎች ቆጠራ አካሂደው ውጤት ባለማሳወቃቸው ከፍተኛ ቅሬታ ቀርቦባቸዋል።
የናይጄሪያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በርካታ የምርጫ ጣቢያዎች በወቅቱ አለመከፈታቸውንም አሳውቋል።
በዘንድሮው የናይጄሪያ ምርጫ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግጭቶች ቢከሰቱም እንዳለፉት ምርጫዎች የገዘፈ አልነበረም ተብሏል።