በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው ባለው የኮፕ28 ስብሰባ ላይ ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ የሚረዱ በርካታ ስምምነቶች ተደርሰዋል
ናይጄሪያ 22 በመቶ የሚሆነውን የደን ሽፋኗን ማጣቷ ተገለጸ
የናይጄሪያ የአካባቢ ሚኒስትር ዶክተር ኢሳቅ ሳሎኮ ሀገሪቱ 22 በመቶ የደን ሽፋኗን ማጣቷን እና በአሁኑ ወቅት 10 ሚሊዮን ችግኞች መትከሏን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ እንደገለጹት ችግኝ መትከል ለኢኮሲስተም ጠቃሚ ስለሚሆን በሚቀጥሉት ሶስት አመታት 10 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል የተያዘው እቅድ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል።
ሚኒስትሩ ለኮፕ28 ስብሰባ በዱባይ በተገኙበት ወቅት ከኢምሬትስ ዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ናይጄሪያ ለሀይድሮ ካርበን ብክለት ትሪትመንት ፕሮጀክት 1 ቢሊዮን ዶላር መመደቧን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በኒጀር ዴልታ ቀጣና የማንግሩቭ ሽፋንን ከፍ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።
የማንግሩቭ ሽፋን በሰው እንቅስቀሴ በተለይም በነዳጅ ፍለጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን የገለጹት ሚኒስትሩ ሀገሪቱ በ10 አመት ውስጥ 22 በመቶ የሚሆን የደን ሽፋን አጥታለች ብለዋል።
በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው ባለው የኮፕ28 ስብሰባ ላይ ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ የሚረዱ በርካታ ስምምነቶች ተደርሰዋል።
በስብሰባው ላይ 198 ሀገራት እና ትላልቅ አለምአቀፍ ተቋማት ተሳትፈዋል።