በናይጄሪያ መስጊድ ተደርምሶ ቢያንስ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ
ሀገሪቱ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያደረግሁ ነው ብላለች
በናይጄሪያ የህንጻ መደርመስ የተለመደ ነው
በናይጄሪያ መስጊድ ተደርምሶ ቢያንስ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ።
በናይጄሪያ ዛሪያ ከተማ አማኞች ጸሎት ላይ እያሉ መስጊድ ተደርምሶ በትንሹ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
አርብ በደረሰው አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መስጊድ ውስጥ ነበሩ ተብሏል።
የከተማው ምክር ቤት ቃል አቀባይ በመጀመሪያ የአራት ሰዎች አስከሬን እንደተገኘ አስታውቀዋል።
የነፍስ አድን ባለሞያዎች በፍርስራሹ ውስጥ ባደረጉት ፍለጋ ደግሞ ሦስት አስከሬኖች ተገኝቷል ሲሉ አክለዋል።
የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነም ተነግሯል።
የአካባቢው ኢሚር ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኸን ከአደጋው አንድ ቀን አስቀዶሞ ከመስጊዱ ግድግዳዎች መሰንጠቅ መታየቱን ተናግረዋል።
የተሰነጠቀውን ግድግዳ ለመጠገንም የመሀንዲሶች ቡድን እየተደራጀ ነበር ተብሏል።
መስጊዱ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ እድሜ እንዳለው ይታመናል።
በናይጄሪያ የህንጻ መደርመስ የተለመደ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው ጠቅሷል።