በፈረንጆቹ ጥቅምት 2021 አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት የዲሲፕሊን ጥሰት ፈጽማለች በሚል ምክንያት በኦካግባሬ ላይ ክስ አቅርቦ ነበር
ናይጀሪያዊቷ የአጭር ርቀት ሯጭ ብለሲንግ ኦካግባሬ አምስት አመት ብዛት ያላቸው የተከለከሉ አበረታች መድሃኒቶችን በመጠቀም እንዲሁም አምስት አመት ለአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት ትብብር ባለማሳየቷ በጥቅሉ 10 አመት በዲሲፕሊን ኮሚቴው ከውድድር ታግዳለች፡፡
ጉዳዩን ሲከታተሉ የነበሩት ብቸኛ ዳኛ እስከ ቶኮዩ ኦሎምፒክ ባለው ጊዜ አትሌቷ በርካታ የተከለከሉ መድኃኒቶችን በተደራጀ መልኩ ተጠቅማለች ሲሉ ደምድመዋል፡፡ የዲሲፕሊን ኮሜቴው አትሌቷ አደገኛ የሆነ ባህሪ ስላሳየች ከመደበኛው አራት አመት ቅጣት በላይ ከፍ እንዲል ማድረጉን ጠቅሷል፡፡
በኤሌክትሮኒክ ምስል መውሰድ፣እግድ መጣልን ጨምሮ የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒትን ምርመራ የማካሄድ መብት እንደሚያውቅ የገለጹት ዳኛው፣ አትሌቷ ለምርመራ ባለመተባበሯ የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት ኃላፊነቱን እንዳይወጣ ማድረጓን ይገልጻል፡፡
በዚህ ምክንያት ብቸኛ ዳኛው አትሌቷ ለአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት ባለመተባበሯ፣ዩኒቱ በእሷ ላይ ተጨማሪ የህግ ጥሰቶች ለማወቅ እና በሌሎች ሊፈጸሙ የሚችሉ ጥሰቶችን ለማወቅ የነበረውን እድል በመዝጋቷ ተጨማሪ አምስት አመት እግድ ተጥሎባታል፡፡
"የዲሲፕሊን ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በደስታ እንቀበላለን፤ የ10 አመት እገዳ ሆን ተብሎ እና በተቀናጀ መልኩ ለማጭበርበር ለሚደረጉ ሙከራዎችን ጠንካራ መልእክት ነው። ይህ በእኛ የምርመራ ችሎታ የተመራ እና ከአዎንታዊ ሙከራ በስተጀርባ ያሉትን ሁኔታዎች ለመመርመር ባለን ቁርጠኝነት የተገኘ ውጤት ነው” ሲሉ የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት ኃላፊ ብሬት ክሎቲየር ተናግረዋል።
በፈረንጆቹ ጥቅምት 2021፣ አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት የዲሲፕሊን ጥሰት ፈጽማለች በሚል ምክንያት በኦካግባሬ ላይ ክስ አቅርቦ ነበር፡፡