ስፒሮ በደብዳቤው ሜታ የትዊተር የንግድ ሚስጥሮችን እና ሌሎች ሚስጢራዊ መረጃዎችን የሚያውቁ የቀድሞ የትዊተር ስራተኞችን ቀጥሯል ሲል ከሷል
ትዊተር የሜታ ፕላትሮርም ባስተዋወቀው አዲሱ ትሪድስ ጉዳይ ክስ እንደሚመሰርት የትዊተሩ ጠበቃ አሌክስ ስፒሮ ለሜታው ማርክ ዙከርበርግ በጻፈው ደብዳቤ ገልጿል።
ባለፈው ሮብዕ ትርድስን ያስተዋወቀው ሜታ እስካሁን 30 ሚሊዮን ደንበኞችን ማፍራት ችሏል።
ትሪድስ ኢንስታግራም ጋር የሚተሳር መሆኑ ሜታ ኢንስታግራም ላይ ያሉትን ቢሊዮን ደንበኞች በመጠቀም የኢለን መስኩን ትዊተር ለመወዳደር እየሰራ ነው።
ስፒሮ በደብዳቤው ሜታ የትዊተር የንግድ ሚስጥሮችን እና ሌሎች ሚስጢራዊ መረጃዎችን የሚያውቁ የቀድሞ የትዊተር ስራተኞችን ቀጥሯል ሲል ከሷል።
ትዊተር በፈጠራ ስራዎቹ ላይ ያለውን የባለቤትነት መብት እንደሚያስጠብቅ የገለጸው ስፒሮ ሜታ የትዊትርን የንግድ ሚስጥሮች እና መረጃዎች ከመጠቀም እንዲቆጠብ ጠይቋል።
ሮይተርስ ስፒሮን ጠይቆ መረጃ አለማግኘቱን ገልጿል።
የሜታ ቃል አቀባይ አንዲይ ስቶን በትሪድስ እንደጻፈው በትሪድስ የኢንጅነሪንግ ቡድን ውስጥ አንድም የቀድሞ የትዊተር ሰራተኛ የለም ሲል ክሱን አጣጥሏል።