አዲሱ ፕሬዝዳንት ከከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እስከ ደህንነት ችግር ከባድ የቤት ስራ ይጠብቃቸዋል ተብሏል
ናይጄሪያውያን የፕሬዝዳንት ሙሃማድ ቡሃሪን ተተኪ ለመምረጥ ድምጽ እየሰጡ ሲሆን፤ በርካቶች ቀጣዩ መሪ በአፍሪካ በህዝብ ብዛት አንደኛ ለሆነችው ሀገር ችግር ፈቺ እንዲሆኑ በጥብቅ ይፈልጋሉ ተብሏል።
አዲሱ ፕሬዝዳንት የአህጉሩ የትልቅ ምጣኔ-ሀብት ባለቤቷን ሀገር ለዓመታት ከከፋ ብጥብጥና ችግር በኋላ በአዲስ መንገድ ይመራሉ የሚል ተስፋ አላቸው።
- የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሃሙድ ቡሃሪ ከሀገሪቱ ምርጫ አስቀድሞ አዲስ የሽግግር ስርዓት አዘጋጁ
- ናይጄሪያ ከመንግስት የባንክ ሂሳቦች ገንዘብ ማውጣትን ልትከለክል ነው
እ.አ.አ. በ1999 ናይጄሪያ ከወታደራዊ አገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ ከተቀየረችበት ጊዜ አንስቶ በተካሄዱ ምርጫዎች ዋና እጩዎች ከሁለተሰ ዋና ፓርቲዎች የተውጣጡ ሁለት የፖለቲከኞች ናቸው።
በጡረታ የተገለሉት የጦር ሰራዊት ጄኔራል ቡሃሪ በህገ መንግስቱ የሚፈቀደውን ከፍተኛውን ስምንት ዓመታት ከመሩ በኋላ በአፍሪካ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት አምራች በሆነችው ናይጄሪያ ስርዓትና ደህንነት ለማምጣት የገቡትን ቃል ተግባራዊ ማድረግ አልቻሉም የሚል ትችት አልተለያቸውም።
ከ93 ሚሊዮን በላይ መራጮች ለቀጣዩ ፕሬዝዳንት እና ለብሄራዊ ምክር ቤት ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን፤ 176 ሽህ 600 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል መባሉን ሮይተርስ ዘግቧል።
የምርጫው ሂደት ቀደም ባሉት የናይጄሪያ ምርጫዎች በሁከትና ብጥብጥ የታጀበ ሲሆን፤ በአሁኑም ምርጫ የደህንነት ስጋት አልተለየውም።
አዲሱ ፕሬዝዳንት ከከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ ድህነት እና የኃይል እጥረት፣ የሰሜን ምስራቅ እስላማዊ አመጽ፣ የነዳጅ ስርቆት እና በየቦታው የሚፈጸሙ ወንጀሎችይ የመሰሉ ችግሮችን መታገል የቤት ስራቸው እንደሚሆን ይጠበቃል።
ቡሃሪን ለመተካት በሚደረገው ውድድር የ70 ዓመቱ የቀድሞ የሌጎስ ገዥ ቦላ ቲኒዩብ፣ የ70 ዓመቱ የገዢው ኦል ፕሮግረሲቭስ ኮንግረስ ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የ76 አመቱ ምክትል ፕሬዝዳንት አቲኩ አቡበከር፣ የዋናው ተቃዋሚ ፒፕልስ ዲሞክራቲክ ፓርቲ እና የ61 ዓመቱ የቀድሞ የአናምብራ ግዛት አስተዳዳሪ ፒተር ኦቢ ተፎካካሪ ናቸው።