በናይጄሪያ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊስ የመከላከያ ጦሩ ድጋፍ ሊያስፈልገው እንደሚችል ገለጸ
ከሀሙስ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ በመካሄድ ላይ የሚገኝው ታቃውሞ በአንድዳንድ ከተሞች ወደ አመጽ ተቀይሯል
እስካሁን ድረስ በፖሊስ እና በሰልፈኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል
በናይጄሪያ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊስ የመከላከያ ጦሩ ድጋፍ ሊያስፈልገው እንደሚችል ገለጸ።
በናይጄሪያ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊስ የመከላከያ ጦሩ ድጋፍ ሊያስፈልገው እንደሚችል ገለበናይጄርያ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊስ የመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፍ ሊያስፈልገው እንደሚችል ገለጸ፡፡
የኑሮ ውድነትን እና የነዳጅ ዋጋ መጨመርን በመቃዎም በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ በሚገኝው ተቃውሞ በአንዳንድ ከተሞች ሰልፎቹ ወደ አመጽ በመቀየር ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡
“በናይጄርያ ያለው መጥፎ አስተዳደር ሊያበቃ ይገባል” በሚል መሪ ሀሳብ ለሳምንታት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ቅሰቀሳ ሲደረግበት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ከሀሙስ ጅመሮ ለተከታታይይ አስር ቀናት ለማከናወን እቅድ ተይዞለታል፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መረጃ እስከ ትላንትናው እለት ድረስ በሁለት ቀናት ብቻ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ባሉ ሶስት ከተሞች 13 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
አምነስቲ በመረጃው አክሎም ለሁሉም ግድያዎች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ተጠያቂ መሆናቸውን ገልጾ፤ አንዳንድ ግድያዎቹ ሰልፈኞችን ለመበተን ሆነ ብለው የተፈጸሙ መሆናቸውን ባደረኩት ማጣራት ማረጋገጥ ችያለሁ ብሏል፡፡
ሰልፈኞቹ ከፖሊስ ጋር ከፍተኛ ግጭት ውስጥ በገቡባቸው ዋና ከተማዋ አቡጃ እና ካኖ የተረጋጉ ሁኔታዎች ያሉ ቢመስልም አሁንም ግን ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የሀገሪቱ ፖሊስ ኢንስፔክተር ጄነራል ካዮዲ ኢግቤቶኩን ፖሊስ ህግ እና ስርአትን ለማስከበር ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ ሰላምን ለማስጠበቅ ጥረት እያደረገ ይገኛል። በአንዳንድ ከተሞች ያሉ ከፍተኛ አመጻዎች ግን የወታደሩን ድጋፍ የሚፈልጉ ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል፡፡
ተቃዋሚዎቹ እንዲፈጸሙ የሚፈልጓቸውን 19 ፍላጎቶች በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለዋጋ መናር ዋናውን ድርሻ የሚወስድው የነዳጅ ድጎማ መነሳት ተመልሶ ተግባረዊ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም መንግስት የሚያወጣቸው ያልተገቡ ወጪዎች ኢኮኖሚው ላይ ጫና እያሳደሩ ስለሚገኙ መንግስት የውጭ ቅነሳ ተግባራዊ ማድረግ አለበት ነው ያሉት፡፡
የነዳጅ ድጎማው ከተነሳ ወዲህ የነዳጅ ዋጋ በሶስት እጥፍ የጨመረ ሲሆን በሀገሪቱ የሚገኝው የምግብ የዋጋ ንረት በ በ40 በመቶ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ አመት በሀገሪቱ የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ንረት ከ30 አመታት ወዲህ ከፍተኛው ነው፡፡
ውጥረቱን ለመቀነስ የሀገሪቱ መንግስት ከውጭ ሀገር ስንዴ በማስገባት በጣም ለተቸገሩ ዜጎች አከፋፍሏል፡፡ በተጨማሪም የአነስተኛ የደሞዎዝ ወለልን መነሻ ከፍ እንደሚያደርግም አሳውቋል፡፡
ሆኖም ለሳምንታት “በናይጄርያ ያለው መጥፎ አስተዳደር ሊያበቃ ይገባል” በሚል መሪ ቃል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ጥሪ ሲከናወንበት የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ አላስቆመውም፡፡