ኢሰመኮ በቅርቡ በመተከል በተካሄደው ጭፍጨፋ 207 ሰዎች መገደላቸውን ማስታወቁ ይታወሳል
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከደረሰው ማንነትን መሰረት ካደረገው ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ አራት የክልሉ ምክርቤት አባት ያለመከሰስ መብታቸው መነሳቱን የክልሉ ምክርቤት አስታውቋል፡፡
ም/ቤቱ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔ ላይ ነው፡፡ ም/ቤቱ በጠቅላይ አቃቤ ህግ ያለመከሰስ መብታቸው ይነሳ የተባቱትን አባላት አድጎ አምሳያ፣ሽፈራው ጨሊቦ፣ ግርማ መኒና አረጋ ባልቢድ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቅርቡ በመተከል በተካሄደው ጭፍጨፋ 207 ሰዎች መገደላቸውን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
“በመተከል ዞን በንጹኃን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ የማያመው እና የማያወግዝ ሊኖር አይገባም”ያለው ም/ቤቱ ያለመከስስ መብት የተነሳባቸው አባላቱ ከግድያው ጋር በተገናኘ መሆኑን ገልጿል፡፡
“በዞኑ የተፈጠረው ችግር የከፋ ያደረገው አመራር የተሳተፈበት መሆኑን የጠቆሙት የምክር ቤቱ አባላት” ዞኑን ለማረጋጋት በግድያው በተሳተፉ ሰዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ም/ቤቱ አስታውቋል፡፡ ም/ቤቱ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝቦች በሰላም እንዳይኖሩ እያደረጉ ነው ብሏል፡፡