የጥይት ማርከሻ መድሃኒት የወሰደው ሰው በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አለፈ
ፖሊስ ጥይት የማያስመታ ባህላዊ መድሃኒት ሰሪ ነው ያለውን ግለሰብ በግድያ ወንጀል አስሯል
ፖሊስ ዜጎች በአጉል እምነት ተነሳስተው ህይወታቸውን እንዳያጡ አሳስቧል
የጥይት ማርከሻ መድሃኒት የወሰደው ሰው በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አለፈ፡፡
በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጀሪያ ጥይት የማያስመታ ባህላዊ መድሃኒት መስራት አለመስራቱን የተሞከረበት ሰው ህይወቱ አልፏል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ክስተቱ የተፈጠረው በሰሜናዊ ናይጀሪያ ቦቺ ግዛት ሲሆን አንድ ጥይት ያማያስመታ ባህላዊ መድሃኒት ሰሪ ሰው ገድሏል ተብሏል፡፡
ግድያው የተፈጸመው ይህ ጥያት የማያስመታ ባህላዊ መድሃኒት ሰሪ ግለሰብ የሰራው መድሃኒት መስራት አለመስራቱን ለመሞከር ጥይቱን ወደ ሌላ ሰው በተኮሰበት ወቅት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ጥይቱ የተተኮሰበት ሰውም ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ ፖሊስ ግድያውን የፈጸመውን ሰው ማሰሩን አስታውቋል፡፡
በናይጀሪያ የአንድ ክልል አስተዳዳሪ 47 የሚዲያ አማካሪዎች መቅጠሩ አነጋጋሪ ሆኗል
በናይጀሪያ ጥይት የማስመታ ባህላዊ መድሃኒት ጉዳት እንደሌላው የሚምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው የተባለ ሲሆን በዚህም ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች እየበዙ መጥተዋል ተብሏል፡፡
የናይጀሪያ ፖሊስ ዜጎች ጥይት የማያስመታ መድሃኒት በሚል መጠቀማቸውን እና ገንዘባቸውን በአታላዮች ከመበላት እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡
ሰዎች የገዙት ባህላዊ መድሃኒት ጥይት እንደማያስመታ በማመን ገንዘባቸውን ከማውጣታቸው ባለፈ መስራት አለመስራቱን ለማረጋገጥ በሚተኮስባቸው ጥይት ህይወታቸውን እያጡ መሆኑንም ገልጿል፡፡