የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለመሆን የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት ኒኪ ሀሌይ ተሰናበቱ
ሀሌይ መሰናበታቸውን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዋነኛ ዕጩ መሆናቸው ተረጋግጧል
በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር የፊታችን ሕዳር ይወዳደራሉ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለመሆን የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት ኒኪ ሀሌይ ተሰናበቱ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ በቀጣዩ ዓመት ሕዳር ወር ላይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች፡፡
በዚህ ምርጫ ላይ የሀገሪቱ ዋና ፓርቲዎች ሪፐብሊካን እና ዲሞክራት የተባሉ ፓርቲዎች አንድ አንድ ዕጩዎቻቸውን ለማቅረብ የእርስ በርስ ፉክክር ሲያካሂዱም ቆይተዋል፡፡
ዲሞክራት ፓርቲ ስልጣን ላይ መሆኑን ተከትሎ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ተፎካካሪዎች አራት የነበሩ ሲሆን በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ኒኪ ሀሌይ መካከል ብርቱ ፉክክር ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ኒኪ ሀሌይ ዶናልድ ትራምፕን ለመፎካከር ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት እንዳቋረጡ አስታውቀዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ እስካሁን በተካሄዱ 15 ግዛቶች በ14ቱ ማሸነፋቸውን ተከትሎ በቀጣዩ ሕዳር በሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ በስልጣን ላይ ካሉት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ይፋለማሉ፡፡
ትራምፕ ሩሲያ የኔቶ አባል ሀገራትን እንድታጠቃ “እንደሚያበረታቱ” ተናገሩ
ኒኪ ሀሌይ ከውድድሩ መሰናበቷን አስመልክታ በሰጠችው መግለጫ ባደረገችው ነገር እንደማትጸጸት የፓርቲያችን ድጋፍ የሌላው ዶናልድ ትራምፕ ለፕሬዝዳንትነት ይወዳደራል ብላለች፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በተደጋጋሚ ኒኪ ሀሌይን በመተቸት አስተያየት የሰጡ ሲሆን ሀሌይ የፕሬዝዳንት ባይደን አራራጭ እንጂ ምርጫውን የማሸነፍ ፍላጎት እንደሌላት ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ ለዩክሬን ተጨማሪ ጦር መሳሪያ ድጋፍ ልትሰጥ ይገባል በሚል አቋማቸው የሚታወቁት ኒኪ ሀሌይ ሰላም የሚመጣው ሩሲያ ስትሸነፍ ነውም ብለዋል፡፡