የቀድሞው የተመድ አሜሪካ አምባሳደር ኒኪ ሀሌይ በዶናልድ ትራምፕ ተበልጠው ከፕሬዝዳንታዊ ውድድር ውጭ መሆናቸው ይታወሳል
ኒኪ ሀሌይ በእስራኤል ቦምብ ላይ “ጨርሷቸው” ስትል ጸፋች፡፡
ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ የነበሩት ኒኪ ሀሌይ በእስራኤል ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በሰሜናዊ እስራኤል ሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ ጉብኝት አድርገዋል የተባሉት ኒኪ ሀሌይ በእስራኤል ጦር መሳሪያ ላይ “ጨርሷቸው” ብለው በእጃቸው ሲጸፉ የሚያሳየው ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭተዋል፡፡
ሀሌይ ጉብኝታቸውን ከቀድሞው በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ዳኒ ዳኖን ጋር አካሂደዋል የተባለ ሲሆን ኒኪ ሀሌይ ሲጽፉ የሚየሳየውን ፎቶ ያነሳቸውም ራሱ አምባሳደር ዳኖን እንደሆነ አልአረቢያ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ዳኒ ዳኖስ “ጨርሷቸው” የሚለውን ፎቶ ካጋራ በኋላ “እዩ የቀድሞ የአሜሪካ ተመድ አምባሳደር እንደምትጽፍ “ሲል በኤክስ ወይም ትዊተር ገጹ ላይ አጋርቷል፡፡
የ52 ዓመቷ ኒኪ ሀሌይ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ለመፎካከር በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ የፓርቲያቸው የመጨረሻ እጩ ለመሆን ከዶናድ ትራምፕ ጋር የተወዳደሩ ቢሆንም ተበልጠው ከውድድሩ ተሰናብተዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ኒኪ ሀሌይን በተደጋጋሚ የተቹ ሲሆን ምክትል ፕሬዝዳንት የማድረግ እቅድ እንደሌላቸውም ተናግረዋል፡፡
እስራኤል በራፋህ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 35 ሰዎች ተገደሉ
ከሰባት ወራት በፊት የተጀመረው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከ36 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል፡፡
ከእስራኤል በኩል 1 ሺህ 200 ዜጎች ሲገደሉ በሀማስ ታግተው ከተወሰዱ 252 ዜጎች መካከል 121 ያህሉ መገደላቸው ተገልጿል፡፡
በትናንትናው ዕለትም የእስራኤል ጦር በራፋህ መጠለያ ጣቢያ ላይ ባደረሰው ጥቃት ንጹሃን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን አምናለች፡፡
ይህን ተከትሎ የአሜሪካ ፖለቲከኞችን ጨምሮ በመላው ዓለም ውግዘቶችን አድርሶባታል፡፡