ደቡብ ሱዳን ከአባልነት ለመሰረዝ ምክንያት የሆነውን የ9 ሚሊዮን ዶላር መዋጮ ከፈለች
ደቡብ ሱዳን ለአፍሪካ ህብረት መክፈል ያለባትን ዓመታዊ ክፍያ ባለመክፈሏ ከአባልነት ሰርዟት ነበር
ደቡብ ሱዳን ለአፍሪካ ህብረት መክፈል ያለባትን የ9 ሚሊዮን ዶላር መዋጮ መክፈሏን ምክትል አምባሳደሩ አስታውቀዋል
ደቡብ ሱዳን ለአፍሪካ ህብረት መክፈል ያለባትን የ9 ሚሊዮን ዶላር መዋጮ መክፈሏን ምክትል አምባሳደሩ አስታውቀዋል
ደቡብ ሱዳን ለአፍሪካ ህብረት የሚጠበቅባትን የ9 (ዘጠኝ) ሚሊዮን ዶላር አመታዊ መዋጮ መክፈሏን በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ምክትል አምበሳደር ዴቪድ ደንግ ለአል ዐይን አማርኛ አረጋግጠዋል፡፡
ደቡብ ሱዳን አባል ለሆነችበት የአፍሪካ ሕብረት መክፈል ያለባትን ዓመታዊ መዋጮ አለመክፈሏን ተከትሎ መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው አህጉራዊው ተቋም ሀገሪቱን ከሕብረቱ አባልነት ሰርዟት ነበር፡፡
ምክትል አምባሳደሩ እንዳሉት ክፍያው በመፈጸሙ ደቡብ ሱዳን ወደ አባልነትለመመለስ ሂደት ላይ መሆኗን ገልጸዋል፡፡
ሕብረቱ ከ2 ዓመት በፊት ባወጣው መመሪያ፣ ከውጭ ሀገራት እና ተቋማት ተጽዕኖ ለመላቀቅ በሚል ማንኛውም የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገር የተጣለበትን ዓመታዊ ክፍያ እንዲከፍል እና ይህ ካልሆነ ከአባልነት እንዲታገድ ወስኖ ነበር፡፡
ደቡብ ሱዳን እንደ አውሮፓውያኑ ሐምሌ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ነው የአፍሪካ ህብረት 54ኛ ሆና ነው የአፍሪካ ህብረትን የቀላቀለችው፡፡ ደቡብ ሰዱን ከሱዳን ተገንጥላ እውቅና ሲሰጣት በአፍሪካ “ወጣት” ሀገር ተብላለች፡፡