የጸጥታው ምክርቤት ፍልስጤም ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ሳይስማማ ቀረ
የፍልስጤም አስተዳደር ሙሉ የተመድ አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበው በ2011 ነበር
የሚያዝያ ወር የምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የማልታዋ አምባሳደር ቫኔሳ ፍራዚየር በተደረገው ዝግ ስብሰባ "ስምምነት የለም" ብለዋል
የጸጥታው ምክርቤት ፍልስጤም ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ሳይስማማ ቀረ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የጸጥታው ምክር ቤት አባላት የፍልስጤም አስተዳደር ባለስልጣን ባቀረበው ሙሉ የተመድ አባልነት ጥያቄ ላይ አልተስማሙም።
ጥያቄውን አዲስ አባል ለሚቀበለው የተመድ ኮሚቴ ያቀረቡት የሚያዝያ ወር የምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የማልታዋ አምባሳደር ቫኔሳ ፍራዚየር በተደረገው ዝግ ስብሰባ "ስምምነት የለም" ብለዋል።
አምባሳደሯ አክለውም እንዳሉት "ነገርግን አብዛኞቹ የአባልነት ጥያቄውን ደግፈውታል።"
አባል ሀገራቱ በጥያቄው አስፈላጊነት ላይ ተስማምተው ቢሆን ኖሮ ለምርጫ ወደ ምክርቤቱ ይቀርብ ነበር።
በተመድ የፍልስጤም ተወካይ ርያድ መንሱር የጸጥታ ምክርቤት የሙሉ አባልነት ጥያቄያችንን በመቀበል አለምአቀፉ መግባባት የተደረሰበትን የ'ቱ ስቴት ሶሉሽንን' ለመፈጸም ቁርጠኛ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረው ነበር።
ፍልስጤም ከ12 አመታት በፊት በመተድ የታዛቢነት ቦታ ተሰጥቷታል።
የፍልስጤም አስተዳደር ሙሉ የተመድ አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበው በ2011 ነበር።
በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኢርዳን ፍልስጤም ለእስራኤል የደህንነት ስጋት ነች ሲሉ ጥያቄውን አስቀድመው ተቃውመዋል።
አምባሳደሩ ለእስራኤል የሀገርነት እውቅና መስጠት የተመድን ቻርተር የሚጥስ እና በድርድር ዘላቂ መፍትሄ እንዳይመጣ የሚያደርግ ነው ሲሉ ተቃውመዋል።
የአረብ ሀገራት ከእስራኤል ጎን የፍልስጤም ሀገር ማቋቋም የሚያስችለው 'የቱ ስቴት ሶሉሽን' ተግባራዊ ካልሆነ በመካከለኛው ምስራቅ ዘላቂ ሰላም አይመጣም የሚል አቋም ይዘዋል።