የጸጥታው ም/ቤት ፍልስጤም ያቀረበችውን ማመልከቻ በዚህ ወር እንደሚመክርበት ተገለጸ
የፍልስጤም አስተዳደር በ2011 ያቀረበውን ሙሉ የተመድ አባልነት ጥያቄ በድጋሚ እንዲያየው ለተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አቅርቧል
የተመድ የጸጥታው ምክርቤት ፍልስጤም የተመድ ሙሉ አባል ለመሆን ያቀረበችውን ማመልከቻ ለሚመለከተው ኮሚቴ መምራቷል
የጸጥታው ም/ቤት ፍልስጤም ያቀረበችውን ማመልከቻ በዚህ ወር እንደሚመክርበት ተገለጸ።
የተባበሩት መንግስታት(ተመድ) የጸጥታው ምክርቤት ፍልስጤም የተመድ ሙሉ አባል ለመሆን ያቀረበችውን ማመልከቻ ለሚመለከተው ኮሚቴ መምራቷል።
የምክርቤቱ ፕሬዝደንት የፍልስጤም አስተዳደር ያቀረበውን የተመድ ሙሉ አባል የመሆን ማመልከቻ አዲስ አባል ለሚቀበለው የተመድ ኮሜቴ በትናንትናው እለት መመራቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
- ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠት ለፈረንሳይ እንደነውር መታየቱ ማብቃቱን ፕሬዝደንት ማክሮን ተናገሩ
- ሀማስ እስራኤል ያቀረበችውን የተኩስ አቁም ምክረ ሀሳብ ውድቅ አደረገ
የማልታ የተመድ አምባሳደር ቫኔሳ ፍራዚየር ኮሜቲው ማመልከቻውን ለማየት ትናንት ከሰአት እንዲሰበሰብ ሀሳብ ማቅረባቸውን እና በዚህ ወር ውይይት እንደሚያደርግበት ገልጸዋል።
ማልታ የምክር ቤቱ የሚያዝያ ወር ፕሬዝደንት ነች።
በተመድ የፍልስጤም ተወካይ ርያድ መንሱር የጸጥታ ምክርቤት የሙሉ አባልነት ጥያቄያችንን በመቀበል አለምአቀፉ መግባባት የተደረሰበትን የ'ቱ ስቴት ሶሉሽንን' ለመፈጸም ቁርጠኛ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። ፍልስጤም ከ12 አመታት በፊት በመተድ የታዛቢነት ቦታ ተሰጥቷታል።
የፍልስጤም አስተዳደር በ2011 ያቀረበውን ሙሉ የተመድ አባልነት ጥያቄ በድጋሚ እንዲያየው ለተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አቅርቧል።
15 አባላት ያሉት ምክር ቤቱ ማመልከቻው አባል ለመሆን የሚያስፈልገውን መስፈርት ማሟላቱን ይገመግማል። ከግመገማው በኋላ በቂ ሆኖ ከተገኘ ለውሳኔ በምክር ቤቱ ይቀርባል።
የአባልነት ጥያቄው የሚጸድቀው ቢያንስ ዘጠኝ አባላት ሲደግፉት እና ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ካልተቃወሙት ብቻ ነው።
በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኢርዳን ፍልስጤም ለእስራኤል የደህንነት ስጋት ነች ሲሉ ተናግረዋል።
አምሳደሩ ለእስራኤል የሀገርነት እውቅና መስጠት የተመድን ቻርተር የሚጥስ እና በድርድር ዘላቂ መፍትሄ እንዳይመጣ የሚያደርግ ነው ሲሉ ተቃውመዋል።
የአረብ ሀገራት ከእስራኤል ጎን የፍልስጤም ሀገር ማቋቋም የሚያስችለው 'የቱ ስቴት ሶሉሽን' ተግባራዊ ካልሆነ በመካከለኛው ምስራቅ ዘላቂ ሰላም አይመጣም የሚል አቋም ያራምዳሉ።