በእስራኤል ውስጥ ፍልስጤማውያን በሚበዙባት በቃ አል ጋርቢ የተወለደው ደቃ በእስራኤል እስር ቤት 38 አመታት አሳልፏል
ፍልስጤማዊው "የነጻነት ታጋይ" በእስራኤል እስር ቤት ህይወቱ አለፈ።
ፍልስጤማዊው ገጣሚ እና የመብት ተማጋች ዋሊድ ደቃ ባደረበት ጽኑ የካንሰር ህመም ምክንያት በእስራኤል ሻሚር ሜዲካል ሴንተር ህይወቱ ማለፉን የመካከለኛው ምስራቅ መገናኛ ብዙኻን የፍልስጤም የእስረኞች እና የቀድሞ እስረኞች ጉዳይ ኮሚሽንን ጠቅሰው ዘግበዋል።
በእስራኤል ውስጥ ፍልስጤማውያን በሚበዙባት በቃ አል ጋርቢ የተወለደው ደቃ በእስራኤል እስር ቤት 38 አመታት ማሳለፋቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ኮሚሽኑ ደቃ የሞቱት የእስራኤል እስርቤት አስተዳደር በሚከተለው የታመሙ እስረኞች "በዝግታ የመግደል" ፖሊሲው መሰረት ነው ብሏል።
በጣም ታዋቂ ከሚባሉት የፍለስጤም እስረኞች አንዱ የሆነው ደቃ በሚቀጥለው አመት የእሰርቤት ቆይታውን ያጠናቅቅ ነበር ተብሏል።
የፍልስጤም ዜና አገሌግሎት ደቃ "የነጻነት ታጋይ" ብሎ የገለጸው ሲሆን ሀማስ ደግሞ ሁሉም እስረኞች እስከሚለቀቁ ትግሉን እንደሚቀጥል ቃል ገብቷል።
ሀማስ ባወጣው መግለጫ የደቃ ሞት "የተከሰተው በወራሪዎች እስርቤት ነው"ሲል አስታውሷል።
የእስራእል እስር ቤት ጉዳይ የሚመለከታቸው የእስራኤሉ የቀኝ ዘመም የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር እታማር ቤን ግቪር እስራኤል "ለሽብርተኛ" ሞት እንደማታዝን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሚዲያ ፖስታቸው ደቃ ለሽብርተኛ የሚገባው የሞት ቅጣት የነበረ ቢሆንም የተፈጥሮ ሞት ሞቷል ብለዋል።
እስራኤል የፍለስጤሜውያን እስረኞችን በአግባቡ በማለመያዝ ክስ ይቀርብባታል።
ደቃ የእስራኤል ወታደርን በመግደል ወንጀል ነበር በ1986 የታሰረው።
እስከህልፈተ ህይወቱ ድረስ በእስርቤት ያሳለፈው ደቃ ለልጆች የሚሆኑ እና ሌሎች በርካታ መጽሃፍትን ደርሷል።