ኖርዌያዊው ደራሲ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
ጆን ፎስ የኖቤልን ሽልማት ያሸነፉ አራተኛው የኖርዌይ ጸሀፊ ናቸው
ተጠባቂው የኖቤል የሰላም ሽልማት አርብ ይካሄዳል
ኖርዌያዊው ደራሲ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ።
ኖርዌያዊው ደራሲ ጆን ፎስ በስነ-ጽሁፍ የዘንድሮውን የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።
ደራሲው "ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በሰጡ ጽሁፎችና ተውኔቶች" መሸለማቸውን ሸላሚው ድርጅት አስታውቋል።
ፎስ በዓለም ላይ በጣም ስመ ገናና ከሆኑ የቲያትር ደራሲዎች አንዱ ሲሆኑ፤ በስራቸው ሰፊ ዘውጎችን ይዳሰሳሉ።
ተውኔት፣ ልብወለድ፣ የግጥም ስብስብ፣ ድርሰት፣ የህጻናት መጽሃፍ እና ትርጉሞችን ጨምሮ የተለያዩ ዘውጎች ላይ አሻራቸውን አስፍረዋል።
የስዊድን አካዳሚ አባል አንደር ኦልሰን እንዳሉት የደራሲው ስራ "ጥልቅ ስሜትን፣ ጭንቀቶችን፣ አለመተማመንና የህይወት እና የሞት ጥያቄዎች ይዳስሳሉ።"
ደራሲው በሀገራቸው የስነ-ጹሁፍ ዘርፍ አንቱታን ያገኙ ሲሆን፤ ለድል ዜናው ለአስር ዓመታት በጥንቃቄ ሲዘጋጁበት እንደነበር ገልጸዋል።
ጆን ፎስ ሽልማቱን እንደሚያሸንፉ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን፤ በሽልማቱ መቆጣጠር የማይችሉት ስሜት እንደተሰማቸው ተናግረዋል።
ደራሲው የኖቤልን ሽልማት ያሸነፉ አራተኛው የኖርዌይ ጸሀፊ ናቸው።
በስዊድን አካዳሚ የሚሰጠው የኖቤል ሽልማት፤ ሰኞ ዕለት በህክምና ዘርፍ በመሸለም ተጀምሯል።
የስነ-ጽሁፍ ሽልማት እንደ ኖቤል የሰላም ሽልማት ሁሉ ልዩ ትኩረት የሚያገኝና የሚያወዛግብ ነው።
የሚጠበቀው የኖቤል የሰላም ሽልማት አርብ ይካሄዳል።