ሶስት ሳይንቲስቶች የፊዚክስ የኖቤል ሽልማት አሸነፉ
ሳይንቲስቶቹ የፈጠሩት 'አልትራ ሾርት ፐልስ' በኦቶሞች ውሰጥ ለውጥ እንዲኖር ስለሚፈጥር የተሻለ የበሽታ ምርመራ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል
በፈረንሳይ የተወለዱት እና በስዊድኑ ለንድ ዩኒቨርሲቲ የሚሰሩት ሊ ሁሊየር የፊዚክስ የኖቤል ሽልማት በማግኘት አምስተኛ ሴት መሆን ችለዋል
ፔሪ አጎስቲኒ፣ ፌረንት ክራውዝ፣ አኔ ሊሁሊየር የተባሉ ሶስት ሳይንቲስቶች የዘንድሮውን የኖቤል የፊዚክስ ሽልማት አሸንፈዋል።
ሳይንቲስቶቹ የፈጠሩት 'አልትራ ሾርት ፐልስ' ቀደም ሲል ከነበረው እጅግ ፈጣን የሆነ እንቅስቃሴ በኦቶሞች ውሰጥ ለውጥ እንዲኖር ስለሚያደርግ የተሻለ የበሽታ ምርመራ ለማካሄድ ያስችላል ተብሏል።
ሽልማቱን ያበረከተው አካዳሚ እንደገለጸው የሳይንቲስቶቹ ጥናት የሰው ልጆች በኦቶሞች ውስጥ ያለውን የኤሌክትሮንስ እንቅስቃሴ የበለጠ እንዲያውቁ ይረዳል።
ይህ ክስተት ለረጅም ጊዜ የማይቻሉ ነው ይባል ነበር። በግኝቱ በኤሌክትሮንስ ውሰጥ ያለው ለውጥ 1/10 በሆነ አቶሰከኔድስ(ከሰከንድ ያነስ የጊዜ መለኪያ) የሚከናወን ክስተት መሆኑ ተገልጿል።
የምርምር ግኝቱ በተለያዩ መስኮች ላይ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።
በኤሌክትሮኒክስ ላይ በምንጠቀምበት ጊዜ፣ ኤሌክትሮንስ በእቃዎች ላይ የሚያሳዩትን ባህሪ መረዳት አስፈላጊ መሆኑን ጥናቱ አስቀምጧል።
ከተሸላሚዎቹ አንዷ የሆነችው ሊሁሊየር ግኝቱን ባቀረቡበት ወቅት "ይህ እጅግ ስመጥር ሽልማት ነው፣ ሽልማቱን በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ" ሲሉ ተናግረዋል።
በፈረንሳይ የተወለዱት እና በስዊድኑ ለንድ ዩኒቨርሲቲ የሚሰሩት ሊ ሁሊየር የፊዚክስ የኖቤል ሽልማት በማግኘት አምስተኛ ሴት መሆን ችለዋል።