ከመቶ አመት በላይ ያስቆጠረው ሽልማት ለአሸናፊዎች 10ሚሊዮን የስዊዲሽ ክሮነር በላይ ይሸልማል
የአሜሪካ፣የፈረንሳይና የኦስትሪያ ሳይንቲስቶች በፊዚክስ የኖቤል ሽልማት አሸንፈዋል።
ሳይንቲስቶች አላይን አስፔክት፣ ጆን ክላውዘር እና አንቶን ዘይሊንገር የተባሉ ሳይቲስቶች የ2022 የኖቤል ሽልማትን በፊዚክስ አሸንፈዋል።
ሽልማቶቹ የተሰጡት "የተጠላላፉ የፎቶኖች ሙከራዎች፣ የቤል እኩልነትን መጣስ እና ፈር ቀዳጅ የኳንተም መረጃ ሳይንስን በማቋቋም" ነው ሲል የሽልማት ሰጪው አካል ማክሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2008 ዓ.ም አስታውቋል።
የሮያል ስዊድን የሳይንስ አካዳሚ ተሸላሚዎቹ ፈረንሳያዊው ሎሬት አስፔክት፣ አሜሪካዊዉ ክላውዘር እና ኦስትሪያዊዉ ዘኢሊንገር ኦስትሪያዊ ለተጨማሪ መሠረታዊ ምርምር እና ለአዲስ ተግባራዊ ቴክኖሎጂ መንገዱን ጠርገዋል።
"አሁን ኳንተም ኮምፒውተሮችን፣ ኳንተም ኔትወርኮችን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የኳንተም ኢንክሪፕትድ ግንኙነትን ያካተተ ትልቅ የምርምር መስክ አለ" ሲል በመግለጫው ተናግሯል።
ከመቶ አመት በላይ ያስቆጠረው ሽልማት ለአሸናፊዎች 10ሚሊዮን የስዊዲሽ ክሮነር በላይ ይሸልማል።
ባለፈው ሳምንት ስዊድናዊው የፖቶሎጂስት ሳይንቲስት ተሸልሟል።