ጃሶን ከ14 ወራት በላይ በቬንትሌተር ታግዞ ሲተነፈስ እንደነበረ ተነግሯል
በራሱ ፈቃድ ሞትን የመረጠው እንግሊዛዊው የረዥም ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ ጃሶን ኬልክ ጉዳይ አነጋገሪ ሆኗል።
የ49 ዓመቱ እንግሊዛዊ ጃሶን በኮሮና ቫይረስ ተይዞ ከ14 ወራት በላይ በቬንትሌተር ታግዞ ሲተነፈስ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም ሞትን መምረጡ ተሰምቷል።
ጃሶን ሞትን የመረጠው ሲቃዩ ሲበዛበት እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፤ “የመተንፈሻ ቬንትለተሩን ንቀሉልኝ” በማለት ይማጸን እንደነበርም ተነግሯል።
ታማሚው ቬንትለተሩ አንዲነቀልለት ካስደረገ በኋላ ትንፋሹ እየተዳከመ በመምጣቱ ከአንድ ሰዓት ተኩል በኋላ ህይወቱ ሊያልፍ እንደቻለም ነው ስካይ ኒውስ የዘገበው።
የጃሶን ባለቤት ቬንትለተሩን እንዳያስነቅለው ብትማጸነውም “መሞት እፈልጋለሁ” ሲላት እንደነበር ከህልፈቱ በኋላ ተናግራለች።
ይሁን እንጂ ከነበረበት ሲቃይ አንጻር የጃሶን ውሳኔ "የጀግና ውሳኔ ነው" ስትል አወድሰዋልች።
ጃሶን ኬልክ የኮሮና ቫይረስ ብሪታንያ ከተከሰረ ጊዜ ጀምሮ በበሽታው ሲሰቃይ የነበረ ሲሆን፤ እስካሁንም ቬንተለተር ሳይነቀልለት ለረጅም ጊዜ ቆይቷል።
ጃሶን በሊድስ ከተማ በሚገኘው በሴይንት ጄምስ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናውን ሲከታተል እንደነበረም ነው ተነገረው።