ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ በባህር ድንበር አቅራቢያ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ተለዋወጡ
የሰሜን ኮሪያ ተደጋጋሚ የጦር መሳሪያ ሙከራ በቀጠናው ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል
ሀገራቱ ከተኩስ ልውውጥ በዘለለ ወደ ጦርነት ስለመግባታቸው የተባለ ነገር የለም
ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ ያደረገችው የሚሳዔል ማስቀንጨፍ ሙከራን ተከትሎ በሁለቱም ኮሪያዎች ግጭት ሊፈጠር እንደሚችል ሲዘገብ ቆይቷል።
እናም ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ በዛሬው እለት በአወዛጋቢው የባር ድንበር አከባቢ ማስጠንቀቂያ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው እየተገለጸ ነው።
የደቡብ ኮሪያ የባህር ሃይል ዛሬ ጠዋት የባህር ድንበር ጥሳ የገባቸውን የሰሜን ኮሪያ የንግድ መርከብ ለመመከት የማስጠንቀቂያ ጥይቶችን መተኮሱን ሮይተርስ የሴኡል ወታደራዊ አዛዦችን በመጥቀስ ዘግቧል።
የደቡብ ኮሪያን ምክንያት ውድቅ ደረገው የሰሜን ኮሪያ ጦር በበኩሉ የባህር ዳርቻው የመከላከያ ሰራዊት “የባህር ኃይል ጠላት እንቅስቃሴ ወደ ሚገኝበባቸው” ስፍራ የማስጠንቀቂያ ተኩስ በመተኮስ ምላሽ መስጠቱ አስታውቋል።
እስካሁን በሁለቱም ኮሪያዎች መካካል ጦርነት መደረጉ የሚያመላክቱ ሪፖርቶች ባይኖሩም በኮሪያ ባረ ሰላጤ ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ ያለው የባህር ድንበር ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ደህንነት ስጋት ምንጭ መሆኑ ይታወቃል።
ሰሜን ኮሪያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የምታስቀነጨፍቸው የባላስቲክ ሚሳዔል ቀጠናውን ወደለየለት ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዳይወስደው ተሰግቷል።
ፒዮንጊያን የሚሳዔል ሙከራዎቹ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ለሚያካሂዱት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት የሚደረግ ነው ብትልም፤ ድርጊቱ በተለይም ደቡብ ኮሪያንና ጃፓንን ስጋት ውስጥ መክተቱ አልቀረም።
በሁኔታው የተደናገጠው የጸጥታው ምክር ቤትም ቢሆን በሰሜን ኮሪያ ላይ ተጨማሪ ማእቀቦች ለመጣል በተላያዩ ምክረ ሀሳቦች ዙሪያ ሲመክር ይስተዋላል።
በፒዮንጊያንግ ላይ ማዕቀብ ለመጣል በቅርቡ ባደረገው ስብሰባም ቻይና እና ሩሲያ መቃወማቸው አይዘነጋም።
በዚህ የተበሳጨችው አሜሪካ፤ ቻይና እና ሩሲያ ማእቀቦችን በመቃወም ለሰሜን ኮሪያ ከለላ እየሰጡ ነው ስትል መውቀሷንም ጭምር የሚታወስ ነው።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገሪቱን ኒውክሌር የታጠቀች ሀገር ብለው በቅርቡ ማወጃቸው ይታወቃል።