አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ለምታስቀነጨፈው ሚሳዔል “ጠንካራ ምላሽ ለመስጠት” ከአጋሮቿ ጋር እየመከርኩ ነው አለች
ሰሜን ኮሪያ በጃፓን የአየር ክልል በኩል አዲስ የባላስቲክ ሚሳዔል ወደ ፓሲፊክ ውቂያኖስ መተኮሷ ተሰምቷል
የአሜሪካ ኢንዶ-ፓስፊክ ኮማንድ የፒዮንጊን ድርጊት አወግዟል
አሜሪካ ሰ ሰ ኮሪያ ለምታስወጭነፈው ሚሳዔል “ጠንካራ ምላሽ ለመስጠት” ከአጋሮቼ ጋር እየመከርኩ ነው አለች፡፡
የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ከደቡብ ኮሪያ እና ከጃፓን አቻዎቻቸው ጋር ሰሜን ኮሪያ በጃፓን ላይ ስለጣለችው ሚሳኤል በተናጠል በስልክ መነጋገራቸውን የዋይት ሃውስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
"በሁለቱም የስልክ ንግግሮች የሀገራቱ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪዎች ተገቢ እና ጠንካራ የጋራ እና ዓለምአቀፍ ምላሾች ላይ ምክክር አድርገዋል እንዲሁም የብሄራዊ ደህንነት አማካሪው ጄክ ሱሊቫን አሜሪካ የጃፓን እና ደቡብ ኮሪያን ለመከላከል ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል"ም ነው ያለው መግለጫው፡፡
ሰሜን ኮሪያ በዛሬው እለት በጃፓን ላይ መካከለኛ ርቀት ያለው ባለስቲክ ሚሳኤል በመተኮሷ ቶኪዮ የሀገሪቱን የሚሳዔል ማንቂያ ሲስተም እንዲሰራ እና ሰዎች እንዲጠለሉ አዛለች።
በሌላ መግለጫ የአሜሪካ ኢንዶ-ፓስፊክ ኮማንድ የፒዮንጊያንግ ድርጊት አውግዟል፡፡
"አሜሪካ እነዚህን ድርጊቶች ታወግዛለች እንዲሁም ሰሜን ኮሪያ ተጨማሪ ህገ-ወጥ እና አለመረጋጋትን ከሚፈጥሩ ድርጊቶች እንድትታቀብ እንደጠይቃለን" ሲልም አስጠንቅቋል ኮማንዱ፡፡
ኒውክሌር ታጣቂ ሀገር የሆነችው ሰሜን ኮሪያ በጃፓን የአየር ክልል በኩል አዲስ የባላስቲክ ሚሳዔል ወደ ፓሲፊክ ውቂያኖስ መተኮሷ ተሰምቷል።
ሀገሪቱ ትናንት ያካሄደችውን የባላስቲክ ሚሳዔል የማስወንጨፍ ሙከራ ጨምሮ ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሰሜን ኮሪያ በጃፓን ሰማይ ላይ ያስወነጨፈችው የባላስቲክ ሚሳዔልን የጃፓን የባህር ድንበር ጠባቂዎች እና የደቡብ ኮሪያ የጥምር ጦር አዛዥ ቀድመው እንደለዩት አስታውቀዋል።
ይህንን ተከትሎም ለጃፓናውያን መጠለያዎች ውስጥ እንዲሸሸጉ የጥንቃቄ መልእክት እንዲደርሳቸው መደረጉ ተነግሯል።
እንዲሁም የባላስቲክ ሚሳዔሉ ጃፓንን እስኪያልፍ ድረስ በሰሜን ምስራቅ ጃፓን በሚገኙት ሆካይዶ እና ኦሞሪ ክልሎች የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በጊዜያዊነት እንሰዲቆም ተደርጎ ነበር።
ሰሜን ኮሪያ በጃፓን አየር ክልል ላይ ሚሳዔል ስታስወነጭፍ ከፈረንጆቹ 2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።
የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ፤ የሰሜን ኮሪያን ተግባር ያወገዙ ሲሆን፤ ተግባሩንም “አረመኔያዊ ድርጊት” ሲሉ ኮንነውታል።
የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሱክ ዬዎል በበኩላቸው፤ የሰሜን ኮሪያ የባላሲቲክ ሚሳዔል መተኮስን ተከትሎ ከባድ ምላሽ ሊሰጥ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።