ፒዮንግያንግ “ሚሳዔችን ያስወነጨፍኩት ለአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አፀፋ ለመስጠት ነው” ብላች
ሰሜን ኮሪያ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ስድስተኛ የባላስቲክ ሚሳዔል በዛሬው እለት ማስወነጨፏ ተገለፀ።
ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ማለዳ ላይ ሁለት የአጭር ርቀተ የባላስቲክ ሚሳዔሎችን ወደ ጃፓን አቅጣጫ ማስወንጨፏን ሮይተርስ ዝግቧል።
ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ በጋ ባወጡት መግለጫ፤ ሰሜን ኮሪያ ሌሊት ላይ የባላስቲክ ሚሰዔሎችን ማስወንጨፏን አረጋግጠው፤ የመጀመሪያው ሚሳዔል ከመሬት በ100 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ 350 ኪሎ ሜትር ገደማ ከበረረ በኋላ መውደቁን አስታውቀዋል።
ሁለተኛው የባላስቲክ ሚሳዔል ደግሞ ከመሬት በ50 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ 800 ኪሎ ሜትር ገደማ ከተጓዘ በኋላ መውደቁን አረጋግጠዋል።
ሰሜን ኮሪያ በትናንትናው እለት እንዳስታወቀችው የሰሞኑ የሚሳዔል ማስወንጨፍ ሙከራዎች አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ላካሄዱት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቃለች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ሰሜን ኮሪያ በሳለፍነው ማሰኞ በጃፓን የአየር ከልል ላይ አደገኛ የሆነ የሚሳዔል ማስወንጨፍ ማካሄዷን ተከተሎ አስቸኳይ ስበስባ ጠርቶ ነበረ።
የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኮሪያ ላይ ተጨማሪ ማእቀቦች እንዲጣሉ ምክረ ሀሰብ ቢቀርብም ሩሲያ እና ቻይና ሀሳቡን ውድቅ አድርገዋል።
በዚህ የተበሳጨችው አሜሪካ፤ ቻይና እና ሩሲያ ማእቀቦችን በመቃወም ለሰሜን ኮሪያ ከለላ እየሰጡ ነው ስትል ወቀሳ አቅርባለች።
ኒውክሌር ታጣቂ ሀገር የሆነችው ሰሜን ኮሪያ በጃፓን የአየር ክልል በኩል አዲስ የባላስቲክ ሚሳዔል ወደ ፓሲፊክ ውቂያኖስ መተኮሷ ይታወሳል።
ሰሜን ኮሪያ በጃፓን አየር ክልል ላይ ሚሳዔል ስታስወነጭፍ ከፈረንጆቹ 2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፤ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ፤ “አረመኔያዊ ድርጊት” ሲሉ ተግባሩን ኮንነውታል።
ሰሜን ኮሪያ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በተከታታይ የሚሳዔል ማስወንጨፍ ሙከራዎችን እያደረገች እንደሆን ይታወቃል።
ፒዮንግ ያንግ ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት ላይ የነበሩት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ ሴኡልን ለቀው ከወጡ ከሰዓታት በኋላ ሚሳዔሎችን መተኮሷ ይታወሳል።