ሰሜን ኮሪያ የተከሰከሰ የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ድሮን አገኘሁ አለች
ሰሜን ኮሪያ አና ደቡብ ኮሪያ አንጃቸው በሌላኛው ላይ ድሮን በማብረር ሲካሰሱ ይደመጣሉ
ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ ደቡብ ኮሪያ በራሪ ወረቀቶችን የያዘ ደሮን በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ አብርራለች የሚል ክስ ማቅረቧ ይታወሳል
ሰሜን ኮሪያ የተከሰከሰ የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ድሮን አገኘሁ አለች።
ሰሜን ኮሪያ የተከሰከሰ የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ድሮን ስብርባሪ ማግኘቷን በትናትናው እለት አስታውቃለች።
ሰሜን ኮሪያ አና ደቡብ ኮሪያ አንጃቸው በሌላኛው ላይ ድሮን በማብረር ሲካሰሱ ይደመጣሉ።
ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ ደቡብ ኮሪያ በራሪ ወረቀቶችን የያዘ ደሮን በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ አብርራለች የሚል ክስ ያቀረበች ሲሆን ይህም በኮሪያ ባህረሰላጤ ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ አድርጎታል።
"የድሮኑ ቅርጽ፣ የበረራ ጊዜው፣ በድሮኑ ስር የተገጠመው የበራሪ ወረቀቶች መበተኛ ሳጥን እና የመሳሰሉት ሲታይ፣ በፒዮንግያንግ መሀል ከተማ በማዘጋጃ ቤት ላይ በራሪ ወረቀት የበተነው ድሮን የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። ነገርግን ገና ድምዳሜ ላይ አልተደረሰም"ሲል ሮይተርስ ኬሲኤንኤን ጠቅሶ ዘግቧል።
የደቡብ ኮሪያ ጦር ድሮን ስለማብረሩ፣ በሀገሪቱ ጦር ወይም በግለሰቦች ስለመላኩ አስተያየት ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ጦሩ ሰሜን ኮሪያ ለሰጠችው አስተያየት ምላሽ መስጠት ወጥመዷ ውስጥ መግባት ነው ብሏል።
"የሰሜን ኮሪያ መሬት፣ የአየር እና የውሃ አካል በደቡብ ኮሪያ ከተጣሰ ከፍተኛ ወታደራዊ ትንኮሳ መሆኑን በድጋሚ የሚያረጋግጥ ነው፤ ይህም ጦርነት ማወጅን እና የበቀል እርምጃን ያስከትል" ብሏል ኬሲኤንኤ።
የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአንድ ወገን የሆነው የሰሜን ኮሪያ ውንጀላ ዋጋ እንደሌለው እና ምላሽ እንደማይገባው ገልጿል።
የደቡብ ኮሪያው ህግ አውጭ ዩ ዮንግ ዎን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ሰሜን ኮሪያ አገኘሁት ያለችው ድሮን በደቡብ ኮሪያው ኩባንያ ሱንግው ኢንጂነሪንግ ከተሰራው እና በ2023 ለደቡብ ኮሪያ ጦር ከቀረበው የቅኝት ድሮን ጋር "በጣም የሚመሳሰል" ነው።
ሰንግው በድረ-ገጹ እንዳለው ከፍተኛ የመብረር አቅማቸው አራት ሰአት የሆነ እና በሰአት ከ140 ኪሎሜትር በላይ የሚጋዙ 100 ኤስ-ባት የተባሉ ድሮኖችን ለደቡብ ኮሪያ ጦር መስጠቱን አስታውቋል።
የደቡብ ኮሪያ የድሮን እዝ ባለፈው አመት የሰሜን ኮሪያ ድሮን ለበረራ በተከለከለ ቦታ ከገባ በኋላ ነበር ድሮን እንዲመረትለት ያዘዘው። ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ግንቦት ወር ወደ ደቡብ ኮሪያ ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን ካስወነጨፈች ወዲህ በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ያለው ውጥረት ተባብሷል።