ዘለንስኪ 10ሺ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በዩክሬኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው ሊዋጉ እንደሚችሉ ተናገሩ
ዘለንስኪ የሶስተኛ ሀገር ተሳትፎ ግጭቱን ወደ አለም ጦርነት ሊቀይረው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዝደንት ይህን የተናገሩት የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሽንግተን እና አጋሮቿ ሰሜን ኮሪያ በዩክሬኑ ጦርነት ለሩሲያ የምታደርገውን እርዳታ በጥንቃቄ እየተከታተሉት እንደሆነ ከገለጹ ከአንድ ቀን በኋላ ነው
ዘለንስኪ 10ሺ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በዩክሬኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው ሊዋጉ እንደሚችሉ ተናገሩ።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ 10ሺ የሚሆኑ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከሩሲያ ጎን ሆነው ዩክሬንን ሊወጉ መሰለፋቸውን የሚያሳይ የደህንነት መረጃ እንዳላቸው በትናንትናው እለት ተናግረዋል።
ዘለንስኪ የሶስተኛ ሀገር ተሳትፎ ግጭቱን ወደ አለም ጦርነት ሊቀይረው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
ፕሬዝደንት ይህን የተናገሩት የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኩርት ካምቤል ዋሽንግተን እና አጋሮቿ ሰሜን ኮሪያ በዩክሬኑ ጦርነት ለሩሲያ የምታደርገውን እርዳታ በጥንቃቄ እየተከታተሉት እንደሆነ ከገለጹ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። ነገርገን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወታደሮች ወደ ሰሜን ኮሪያ ተልከዋል የሚለውን የዩክሬን መረጃ አላረጋገጡም።
"ሰሜን ኮሪያ ወታሮች ወደ ዩክሬን መላኳን የሚያሳይ የደህንነት መረጃ አግኝተናል"ሲሉ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
"10ሺ የእግረኛ ተዋጊዎችን አዘጋጅተዋል፣ ነገርግን እስካሁን ወደ ዩክሬን አልተንቀሳቀሱም።"
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ቀደም ብለው ማንኛውም የሰሜን ኮሪያ ተሳትፎ ግጭቱን ወደ "አለም ጦርነት ለመቀየር የመጀመሪያ እርምጃ" ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የኔቶ ዋና ጸኃፊ ማርክ ሩቴ አጋሮች "የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በውጊያው ስለመሳተፋቸው መረጃ የለም። ነገርገን ሰሜን ኮሪያ ሩሲያን በብዙ መልኩ እየደገፈች እንደሆነ እናውቃለን። ይህ በጣም ያስጨንቃል።"
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ሩሲያን ለማሸነፍ ያስችላል ያሉትን "የድል እቅድ" በቤልጅየም ብራሰልስ ተገኝተው ከአውሮፓ ህብረት መሪዎች እና ከኔቶ መከላከያ ሚኒስትሮች በሚወያዩበት ወቅት የአጋሮቻቸውን ድጋፍ ከፍ ያደርግላቸዋል ተብሏል።
ዩክሬን በረጅም ርቀት ሚሳይሎች ሩሲያ ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ እንዲፈቀድላት እና የኔቶ አባል እንድትሆን ግብዣ እንዲቀርብላት የሚሉት የእቅዱ ዋና ነጥቦች ናቸው።
"ዩክሬን 33ኛ የኔቶ አባል ሀገር መሆን ይገባታል፣ ሰለሆነም ይህ እንዲሳካ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" ብለዋል ዘለንስኪ።
"የዩክሬናውያን የጋራ እሴቶቻችን ለመጠበቅ አላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል። ለአውሮፓ ትልቅ ስጋት ከሆነችው ሩሲያ ጋር እየተዋጋን ነው።"
ዩክሬን እና ምዕራባውያን ሀገራት ሰሜን ኮሪያ እና ኢራን በዩክሬኑ ጦርነት ጥቅም ላይ የሚውሉ የጦር መሳሪያዎች ለሩሲያ እየሰጡ ነው የሚል ተደጋጋሚ ክስ ያቀርባሉ።
ሰሜን ኮሪያ እና ኢራን ግን የጦር መሳሪያ ድጋፍ በማድረግ እጃቸው እንደሌለበት በተደጋጋሚ ተናግረዋል።