ሰሜን ኮሪያ 1.4 ሚሊዮን ዜጎቿ ጦሩን ለመቀላቀል ማመልከታቸውን አስታወቀች
ባለፈው አመት የሀገሪቱ መንግስት መገናኛ ብዙሃን አሜሪካን ለመዋጋት 800ሺ ወጣቶች መመዝገባቸውን ይፋ አድርጋ ነበር
ሰሜን ኮሪያ ከዚህ በፊትም በቀጣናው ውጥረቶች በሚያይሉበት ወቅት እንዲህ አይነት መረጃዎችን በመልቀቅ ትታወቃለች
ሰሜን ኮሪያ 1.4 ሚሊዮን ዜጎቿ ጦሩን ለመቀላቀል ማመልከታቸውን አስታወቀች።
ደቡብ ኮሪያን በድሮን ድንበር ጥሳ ትንኮሳ ፈጽማለች የሚል ክስ ያቀረቡት የሰሜን ኮሪያ መገናኛ ብዙሃን 1.4 ሚሊዮን ገደማ ወጣት ሰዎች ጦሩን ለመቀላቀል መመዝገባቸውን በዛሬው እለት ገልጸዋል።
ጦሩን ለመቀላቀል ማመልከቻ ያስገቡት ተማሪዎችን እና የወጣቶች ማህበር አመራሮችን ጨምሮ ወጣቶች ጠላትን ለመደምስስ በሚደረገው "የተቀደሰ ውጊያ" ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ሮይተርስ ኬሲኤንኤን ጠቅሶ ዘግቧል።
ኬሲኤንኤ ይፋ ባልሆነ ቦታ ወጣቶች ማመልከቻቸውን ሲፈርሙ የሚያሳዩ ፎቶዎችን ለቋል።
ሰሜን ኮሪያ በጦሩ ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ 1.4 ሚሊዮን ወጣቶች እንዳሏት ይፋ ያደረገችው በኮሪያ ባህረሰላጤ ያለው ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።
ሰሜን ኮሪያ ከዚህ በፊትም በቀጣናው ውጥረቶች በሚያይሉበት ወቅት እንዲህ አይነት መረጃዎችን በመልቀቅ ትታወቃለች። ባለፈው አመት የሀገሪቱ መንግስት መገናኛ ብዙሃን አሜሪካን ለመዋጋት 800ሺ ወጣቶች መመዝገባቸውን ይፋ አድርጋ ነበር።
በ2017፣ 3.5 ሚሊዮን ሰራተኞች፣ የፓርቲ አባላት እና ወታደሮች ጦሩን መቀላቀላቸው ተዘግቦ ነበር። በሮይተርስ ይህን የሰሜን ኮሪያ መረጃ ለማረጋገጥ አንደማይችል ጠቅሷል።
የስትራቴጂክ ስተዲስ አለምአቀፍ ኢንስቲትዩት መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ሰሜን ኮሪያ 1.28 ወታደሮች እና 600ሺ ተጠባባቂዎች አሏት። ሀገሪቱ አብዛኞቹ ያልታጠቁ 5.7 ሚሊዮን የአርሶ አደር ተጠባባቂ ኃይል እንዳላት ኢንስቲትዩት ገልጿል።
ሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ወታደራዊ ክምችት ባለበት ድንበር ያለውን ሁለቱን ኮሪያዎች የሚያገናኘውን በእሷ በኩል ያለውን የመንገድ እና የባበር መስመር በትናንትናው እለት ማውደማ ውጥረቱ በከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሚያሳይ ነው።
ሰሜን ኮሪያ በድንበር አካባቢ ያለውን ምሽጓን ለማጠናከር ሁለቱን ኮሪያዎች የሚያገናኘውን ሙሉ በሙሉ እንደምታፈርስ አሳውቃ ነበር።
ከ1950-53 የተካሄደው የእርስበርስ ጦርነት ያለሰላም ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ሁለቱ ኮሪያዎች አሁንም ጦርነት ላይ ናቸው በሚያስብል ውጥረት ውስጥ ናቸው።
ሰሜን ኮሪያ ሴኡል ድሮኖችን በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ ላይ በማብረር ያቀረበች ሲሆን ሁለቱ ኮሪያዎች ደግሞ ቆሻሻ የያዙ ፊኛዎችን በመላክ አንዳቸው ሌላኛቸውን ይከሳሉ። የደቡብ ኮሪያ መንግስት ድሮኖቹ በጦሩ ወይም በግል ስለመላካቸው ምላሽ አልሰጠም።
"ጦርነት የሚቀሰቀስ ከሆነ ሰሜን ኮሪያ ከካርታ ትጠፋለች። ጦርነት የምትፈልግ ከሆነ ለማጥፋት ዝግጁ ነን" ሲሉ የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣን መናገራቸውን ኬሲኤን ዘግቧል።