ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የመልሶ መዋሀድ ፖሊሳዋ እንዲቀር አደረገች
ኪም የሰሜን-ደቡብ መልሶ መዋሀድን የሚያሳዩ ምልክቶች በሙሉ እንዲፈርሱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብሏል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሀገሪቱ ህገመንግስት ደቡብ ኮሪያ "ዋነኛ ጠላት" እንዲል ሆኖ እንዲስተካከል ጥሪ አቅርበዋል
ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የመልሶ መዋሀድ ፖሊሳዋ እንዲቀር አደረገች።
ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ለመዋሀድ ያወጣችውን ፖሊሲ ማስቀረቷን አስታውቃለች።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በትናንተናው እለት በተዘጋጀው ትልቅ የህዝብ ስብሰባ ላይ የሀገሪቱ ህገመንግስት ደቡብ ኮሪያ "ዋነኛ ጠላት" እንዲል ሆኖ እንዲስተካከል ጥሪ አቅርበዋል።
በሁለቱ ተቀናቃኞች መካከል ጦርነት የሚቀሰቀስ ከሆነ ህገመንግስቱ ደቡብ ኮሪያን "መውረርን፣ መግዛትን እና መልሶ መቆጠሠጠርን" ማካተት እንዳለበት ኪም ተናግረዋል።
ኪም ጆንግ ኡን ሰሜን ኮሪያ ጦርነት የመጀመር ፍላጎት የላትም፤ ነገርግን የማስቀረት ፍላጎትም የላትም ብለዋል።
ኪም በሟች አባታቸው ኪም ጆንግ ሁለተኛ የተገነባውን 'የናሽናል ሪዩኒፊኬሽን' ሀውልትን ጨምሮ የሰሜን-ደቡብ መልሶ መዋሀድን የሚያሳዩ ምልክቶች በሙሉ እንዲፈርሱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብሏል።
የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ይኦል በዛሬው እለት ከቢኔያቸውን ሰብስበው እንደተናገሩት የሰሜን ኮሪያን ድርጊት "ጸረ ሀገር እና ጸረ-ታሪክ" ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያን የምታጠቃ ከሆነ ከባድ ጥቃት ይገጥማታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የኮሪያ ባህረ ሰላጤ ወደ ሁለት የተከፈለው ለአስርት አመታት የቆየው የጃፖን ቅኝ ግዛት በ1945 ከተጠናቀቀ በኋላ ነበር።
ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳይል ሙከራዋን በማጠናከሯ ምክንያት በሰሜን ኮሪያ እና በደቡብ ኮሪያ መካከል ያለው ውጥረት ከቅርብ አመታት ወዲህ አይሏል።