ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ወደሚያዋስናት ድንበር 200 ሚሳይሎችን አስወነጨፈች
በደቡብ ኮሪያ በሚገኙ ሁለት ደሴቶች ያሉ ነዋሪዎች ባልታወቀ "ሁኔታ" ምክንያት ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል
የደቡብ ኮሪያ ጦር እንዳስታወቀው የሰሜን ኮሪያ ሚሳይል ጥቃት በጦሩም ይሁን በንጹሃን ላይ ጉዳት አላደረሰም
ሰሜን ኮሪያ 200 ሚሳይሎችን ማስወንጨፏ ተገለጸ።
ሰሜን ኮሪያ 200 ሚሳይሎችን በማስወንጨፍ በጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ያሉ ሁለት ደሴት እንዲለቀቁ ማስገደዷን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ባለስልጣን እንደገለጹት ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ወደሚያዋስናት የማሪታይም ድንበር 200 ሚሳይሎችን አስወንጭፋለች።
በደቡብ ኮሪያ በሚገኙ ሁለት ደሴቶች ያሉ ነዋሪዎች ባልታወቀ "ሁኔታ" ምክንያት ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ነዋሪዎችን ለቀው እንዲወጡ ያዘዘው፣በሰሜን ኮሪያ ሚሳይል ተኩስ ምክንያት ወይም መልስ ለመስጠት ለማመቻቸት ስለመሆኑ አልገለጸም።
ነገርግን ከሁለቱ ደሴቶች በአንዱ ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ የደረሳቸው መልእክት የደቡብ ኮሪያ ባህር ኃይል ተኩስ እንደሚያደርግ ያመለክታል።
ውዝግብ ከተፈጠረበት የማሪታይም ድንበር በቅርብ ርቀት የምትገኘው የዮንፒዮንግ ደሴት ባለስልጣን የመልቀቅ ትዕዛዙ የተላለፈው በሲኡል ጦር መሆኑን ገልጸዋል።
ጦሩ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው የሰሜን ኮሪያ ሚሳይል ጥቃት በጦሩም ይሁን በንጹሃን ላይ ጉዳት አላደረሰም።
የሰሜን ኮሪያን ድርጊት "ጸብ አጫሪ" ነው ያለችው ደቡብ ኮሪያ፣ የኮሪያ ባልረሰላጤ ሰላምን ሊያናጋ ይችላል ስትል አስጠንቅቃለች።
በፈረንጆቹ 2010 ሰሜን ኮሪያ ወደ ዮንግፒዮንግ ደሴት ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ከ1953ቱ የኮሪያ ጦርነት ወዲህ ከባድ በተባለ ጥቃት አራት ሰዎችን መግደሏ ይታወሳል።
በወቅቱ ሰሜን ኮሪያ ጥቃቱን የፈጸመችው፣ደቡብ ኮሪያ የቀጥታ ተኩስ ልምምድ በማዶረግ ትንኮሳ ስላደረገች ነው የሚል መልስ ሰጥታ ነበር።