የሰሜን ኮሪያው ኪም የታገዱ ሚሳይሎችን ለሩስያ ሚንስትር አስጎበኙ
የሩሲያና ቻይና ልዑካን የሰሜን ኮሪያን 70ኛ ዓመት "የድል ቀን" ለማክበር ፒዮንግያንግ ገብተዋል
መከላከያ ሚንስትር ሰርጌይ የጎበኟቸው ሚሳይሎች በተመድ የጸጥታው ም/ቤት ውሳኔዎች የተከለከሉ ናቸው
የሰሜን ኮሪያው ኪም የታገዱ ሚሳይሎችን ለሩስያ ሚንስትር አስጎበኙ።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የሩስያ መከላከያ ሚንስትር የመከላከያ አውደ ርዕይ የጎበኙ ሲሆን፤ ሀገራቱ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ ቃል በገቡበት ወቅት የተከለከሉ ሚሳይሎችን መመልከታቸው ተነግሯል።
የሩሲያው መከላከያ ሚንስትር ሰርጌይ ሾይጉ እና የቻይና የፖለቲካ ቢሮ አባልን ጨምሮ የልዑካን ቡድን የኮሪያ ጦርነት ያበቃበትን፤ 70ኛ ዓመት "የድል ቀን" ለማክበር ፒዮንግያንግ ገብተዋል።
ሚሳይሎቹ የተከለከሉት በተመድ የጸጥታው ም/ቤት ውሳኔዎች ሲሆን፤ ሩሲያ እና ቻይና ለውሳኔው ድጋፍ ሰጥተዋል።
በዚህ ሳምንት ከአሜሪካ ጋር ፉክክር ውስጥ የገቡት ሦስቱ ሀገራት አጋርነታቸውን ለማሳየት አስደናቂ የተባለ እርምጃ ተራምደዋል።
ሾይጉ ከሶቪየት ህብረት ውድቀት በኋላ የሩሲያ የመከላከያ ሚንስትር በሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያውን ጉብኝት እያደረጉ ነው።
ለሰሜን ኮሪያ የሩሲያ እና የቻይና ልዑካን መምጣት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ለዓለም የመጀመሪያ ትልቅ መክፈቻ ነው ተብሏል።
ሾይጉ ለኪም ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደብዳቤ መስጠታቸውን የሰሜን ኮሪያ ሚዲያ ዘግቧል።
ኪም ጉብኝቱ በሰሜን ኮሪያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን "ስልታዊ እና ባህላዊ" ግንኙነት የበለጠ ያሳደገ ነው ብለዋል።
ተንታኞች ሾይጉ በሰሜን ኮሪያ የሚሳይል ጉብኝት ማድረጋቸው ሩሲያ የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር መርሃ-ግብር እንድትቀበል የሚያሳይ ነው ብለዋል።