ሰሜን ኮሪያ አሜሪካን የሚያወግዝና የኒውክሌር ጦርነት ማስጠነቀቂያ መልእክት ያዘለ ሰልፍ አካሄደች
120 ሺህ ሰሜን ኮሪያውን የተሳተፉበት ሰልፉ የሁለቱ ኮሪያዎች ጦርነት የተጀመረበት 73ኛ ዓመት መታሰቢያ ነው
በሰልፉ ላይ “የበቀል ጦርነት” አሜሪካን ለማጥፋት የሚሉና ሌሎች መፈክሮች ታይተዋል
ሰሜን ኮሪያ አሜሪካን የሚያወግዝና የኒውክሌር ጦርነት ማስጠነቀቂያ መልእክት ያዘለ ሰልፍ በትናትናው እለት ማካሄዷ ተነግሯል።
በፒዮንግያግ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ሰሜን ኮሪያውያን “የበቀል ጦርነት” አሜሪካን ለማጥፋት የሚሉ እና ሌሎቸ መፈክሮችን ጮክ ብለው ማሰማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
- ሰሜን ኮሪያ በጠላት ላይ "ከፍተኛ ቀውስ" ያስከትላል ያለችውን ሚሳይል መሞከሯን አስታወቀች
- ሰሜን ኮሪያ ጦሯ በየትኛውም ጊዜ የኒዩክሌር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጁ እንዲሆን አሳሰበች
ሰልፉ የሁለቱ ኮሪያዎች ጦርነት የተጀመረበት 73ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ የተካሄደ መሆኑን የሀገሪቱ የመንግስት ሚዲያ ዘግቧል።
በትናንትናው እለት በሰሜን ኮሪያ ዋና ከተማ ፒዮንግያንግ በተካሄደው ሰልፍ ላይ 120 ሺህ ሰራተኞች እና ተማሪዎች መሳተፋቸውንም የሰሜን ኮሪያ የዜና ኤጀንሲ አስታውቋል።
የተለቀቁ ምስሎች ላይም በስታዲየም ውስጥ የነበሩ ሰዎች እጅ “አሜሪካ ሙሉ በሙሉ በእኛ ቀለበት ውስጥ ነች፤ ኢምፔሪያሊስት አሜሪካ የሰላም አውዳሚ ነች” የሚሉ መፈክሮች ታይተዋል።
“ሰሜን ኮሪያ አሁን አሜሪካን ለመቅጣት የሚያስችል ጠንካራ መሳሪያ አላት”፤ በዚህች ምድር ላይ ያሉ ተበቃዮች ጠላትን ለመበቀል በማይበገር ፍላጎት እየተንገበገቡ ነው” የሚሉ መፈክሮችም ታይተዋል።
ኒውክሌር ታጣቂዋ ሰሜን ኮሪያ ትልቁን የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔልን ጨምሮ በርካታ መሳሪያዎችን እየሞከረች ሲሆን፤ ይህም ከደቡብ ኮሪያ እና የደቡብ ኮሪያ አጋር ከሆነችው አሜሪካ ጋር ያለውን ውጥረት እያባባሰው መጥቷል።