ሀገሪቱ በአዲሱ የዓለም ስርዓት መሰረት የዲፕሎማሲ ግንኙነቴን እያስተካከልኩ እንጂ የገንዘብ ችግር ገጥሞኝ አይደለም ብላለች
ሰሜን ኮሪያ በአንድ ወር ውስጥ አምስተኛ ኢምባሲዋን ዘጋች፡፡
ሰሜን ኮሪያ በኔፓል ያለው ኢምባሲዋን የዘጋች ሲሆን ይህም በአንድ ወር ውስጥ አምስተኛው እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ሰሜን ከሪያ በገጠማት ከባድ የገንዘብ እጥረት ምክንያት ኢምባሲዎቿን ለመዝጋት መገደዷን ገልጸዋል፡፡
ከምዕራባዊያን ጋር ቁርሾ ውስጥ ያለችው ሰሜን ኮሪያ ህዝቧን እንኳን መመገብ አቅቷት ለከፋ ድህነት ተዳርጋለች የተባለ ሲሆን ፒዮንግያንግ ግን ይህን ውድቅ አድርጋለች፡፡
የሰሜን ሞሪያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የዓለም ስርዓት እየተቀየረ በመሆኑ የሀገሪቱን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ኢምባሲዎቻችንን እየከፈትን እና እየዘጋን ነው ሲል አስታውቋል፡፡
ሰሜን ከሪያ ከዚህ በፊት በስፔን፣ አንጎላ፣ ኡጋንዳ፣ ሆንግ ኮንግ እና ኔፓል የነበሩ ኢምባሲዎቿን የዘጋች ሲሆን ይህም የዲፕሎማሲ ማስተካከያ ለማድረግ በማለም እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የሃማስ ታጣቂዎች ሰሜን ኮሪያ ሰራሽ መሳሪያዎችን ታጥቀዋል?
ጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ግን የፒዮንግያንግ ድርጊት ለገጠማት ስር የሰደደ የገንዘብ እጥረት ምክንያት እንጂ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ማስተካከያ እንዳልሆነ አስታውቃለች ሲል ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ እና ተመድ በተጣለባት ተደጋጋጋሚ ማዕቀብ ምክንያት ኢኮኖሚዋ ተጎድቷል የተባለ ሲሆን ለዲፕሎማቶቿ ገንዘብ መክፈል ከማትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለችም ተብሏል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ለዲፕሎማሲ ስራዎቿ የተለያዩ ህገወጥ አሰራሮችን ትከተላለች የተባለ ሲሆን አሁን ላይ በመላው ሀገሪቱ የተከሰተው ረሃብ ግን ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ተገከትሎ ኢምባሲዎቿን እስከማዘጋት ማድረሱ ተገልጿል፡፡
ሜን ኮሪያ አሁን ላይ ከሩሲያ እና ቻይና ጋር ያላትን ወዳጅነት እና የትብብር ደረጃን በማሻሻል ላይ መሆኗ ይታወሳል፡፡