ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ ተተኳሽ ሸጣለች የሚለውን የሚዲያ ሪፖርት አስተባበለች
ሰሜን ኮሪያ “በዩክሬን ደም መፋሰስ እና ውድመት እያመጣች ያለችው አሜሪካ ናት” ብላለች
ለሩሲያ ተተኳሽ አልሰጠሁም የምትለው ሰሜን ኮሪያ፤ አሜሪካ ለዩክሬን ገዳይ የጦር መሣሪያዎችን መስጠቷን አውግዛለች
የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ ጥይት አቀረበች የሚለውን የሚዲያ ዘገባ “መሠረተ ቢስ ነው” ሲል አስተባብሏል።
ለሩሲያ ጥይት አልሰጠሁም የምትለው ሰሜን ኮሪያ፤ አሜሪካ ለዩክሬን ገዳይ የጦር መሣሪያዎችን መስጠቷን ማውገዟን ሮይተርስ የሰሜን ኮሪያውን ኬሲኤንኤ የዜና አገልግሎት ጠቅሶ ዘግቧል።
የጃፓኑ ቶኪዮ ሺምቡን ቀደም ብሎ እንደዘገበው ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ወር ድንበሯን አቋርጣ በባቡር ወደ ሩሲያ የጦር መሳሪያ ጥይቶችን ጨምሮ የመድፍ ዛጎሎችን እንደላከች እና በሚቀጥሉት ሳምንታት ተጨማሪ ጭነት እንደሚጠበቅ ገልጿል።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ በኬሲኤንኤ በሰጠው መግለጫ “ ሰሜን ኮሪያ ጥይትን ለሩሲያ አቀረበች የሚለው የጃፓን ሚዲያ የውሸት ዘገባ ውሸች ነው ብላለች።
ዋይት ሀውስ ሐሙስ ዕለት እንዳስታወቀው ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ውስጥ የሚገኙትን የሩስያ ጦር ኃይሎች ለማጠናከር እንዲረዳው ለዋግነር ግሩፕ የግል የሩሲያ ወታደራዊ ኩባንያ የመጀመሪያ ደረጃ ትጥቅ ማስረከብን ማጠናቀቁን አስታውቋል።
የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ስለዋግነር ምንም አልተናገረም።
እንደ ኋይት ሀውስ ገለፃ ዋግነር እግረኛ ሮኬቶችን እና ሚሳኤሎችን ከሰሜን ኮሪያ ወሰደ ፣ምንም እንኳን የዋግነር ባለቤት ኢቭጄኒ ፕሪጎዚን “ወሬ እና ግምት” ሲሉቢያስተባብሉም።
የሰሜን ኮሪያ ቃል አቀባይ በበኩላቸው "በሰሜን ኮሪያ እና በሩሲያ መካከል ባለው 'የጦር መሳሪያ ግብይት' ጉዳይ ላይ በመርህ ላይ ባለው አቋሙ ላይ ለውጥ አላመጣም" ሲል የሰሜን ኮሪያ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ “በዩክሬን ደም መፋሰስ እና ውድመት እያመጣች ያለችው አሜሪካ ናት” ብለዋል ።