ሰሜን ኮሪያ ሁለት ባለስቲክ ሚሳይሎችን ማስንጨፏን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታወቀ
ባለሙያዎች ሰሜን ኮሪያ አሜሪካን ሊመቱ የሚችሉ ሚሳይሎች አሏት የሚል ግምታቸው እየገለጹ ነው
ፒዮንጊያንግ ባለፈው ወር እጅግ የላቀ አህጉር አቀፍ ባለስቲክ ሚሳዔል ማስወንጨፏን የሚታወስ ነው
ሰሜን ኮሪያ ሁለት ባለስቲክ ሚሳይሎችን ማስወንጨፏን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታወቀ፡፡
የደቡብ ኮሪያና አሜሪካ የጋራ ወታደራዊ ኃላፊዎች በትናንትናው እለት ባወጡት መግለጫ ፤ በሰሜን ፒዮንጋን ግዛት ከሚገኘው ከቶንግቻንግ-ሪ አካባቢ የተተኮሱ ሁለት ባለስቲክ ሚሳይሎች ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ሚሳይሎቹ የተተኮሱት ከጠዋቱ 11፡13 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡05 በምስራቅ ባህር ሲሆን ይህም የጃፓን ባህር ተብሎ የሚጠራውን የውሃ አካል ላይ ያነጣጠረ ነበር ተብሏል፡፡
"የእኛ ወታደሮች በቅርበት በመተባበርና የተሟላ ዝግጁነት አቀማመጥን በመጠበቅ ክትትልን እና ጥንቃቄን አጠናክሯል" ብለዋል ወታዳራዊ ኃላፊዎቹ፡፡
ሰሜን ኮሪያ ድርጊቱን የፈጸመችው ከፍተኛ ግፊት ያለው ጠንካራ ነዳጅ ሞተርን ከፈተነች ከቀናት በኋላ ነው መሆኑ ነው፡፡
ይሁን እንጅ የመንግስት ሚዲያዎች “ለሌላ አዲስ አይነት ስትራቴጂካዊ የጦር መሳሪያ ስርዓት ማበልጸጊያ ” ተደረጎ የሚወሰድ አስፈላጊ ሙከራ አድርገው አድርገው በመዘገብ ላይ ናቸው፡፡
አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚገምቱት ሰሜን ኮሪያ በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ ባሳለፈቻት ዓመታት ብዛት መሰረት አሜሪካን በሙሉ ሊመቱ የሚችሉ በኒውክሌር የተደገፉ ሚሳዔሎች አሏት።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር መርሃ ግብር በመቃወም መደበኛ ወታደራዊ ልምምዳቸውን በማስፋፋት የተቀናጀ የመከላከል አቅማቸውን የበለጠ አጠናክረው እንደገፉበት ነው።
ሰሜን ኮሪያም፤ ከአሜሪካ እና ከደቡብ ኮሪያ ጋር ሊፈጠሩ በሚችሉ ግጭቶች የኒውክሌር ጦር መሳሪያን በቅድመ ሁኔታ እንደምትጠቀም ማስፈራራቷ አይዘነጋም፡፡
ፒዮንግያንግ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የጦር መሳሪያ ሙከራ በማድረግ ባለፈው ወር እጅግ የላቀ አህጉር አቀፍ ባለስቲክ ሚሳዔል ማስወንጨፏን የሚታወስ ነው፡፡
ይህም ከአሁኑ ሙከራ ጋር ተዳምሮ በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለው ወታደራዊ ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር እንዳደረገው ይገለጻል፡፡