ሰሜን ኮሪያ ህዝብን ለጎርፍ አደጋ አጋልጠዋል ያለቻቸውን ካድሬዎች በሞት ቀጣች
ሀምሌ ወር ላይ በሰሜን ኮሪያ በተከሰተ ጎርፍ ከ4 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተወስደዋል
ሰሜን ኮሪያ ሀላፊነታቸውን አልተወጡም ያለቻቸውን 30 ካድሬዎች በሞት ቀጥታለች
ሰሜን ኮሪያ ህዝብን ለጎርፍ አደጋ አጋልጠዋል ያለቻቸውን ካድሬዎች በሞት ቀጣች፡፡
ጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ጨምሮ ከሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ጋር መልካ ግንኙነት የሌላት ሰሜን ኮሪያ ሀላፊነታቸውን አልተወጡም ባለቻቸው ካድሬዎች ላይ እርምጃ ወስዳለች፡፡
ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ ከቻይና ጋር አዋሳኝ በሆነችው ቻጋንግ ክልል ላይ ከባድ የጎርፍ አደጋ የደረሰ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል ተብሏል፡፡
እንዲሁም ሲኒጁ የተሰኘችው ሌላኛዋ ክልልም ተመሳሳይ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ አጋጥሞ ነበር፡፡
የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከሆነ ህዝብ በጎርፍ አደጋዎች እንዲጎዳ አስቀድመው የመከላከል ስራዎችን አልሰሩም በተባሉ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ዘግቧል፡፡
መቀመጫውን ደቡብ ኮሪያ ያደረገው ሳውዝ ቲቪ በበኩሉ የዜጎች መኖሪያ ቤቶች፣ የሕዝብ መገልገያ መሰረተ ልማቶች እና ሌሎች ተቋማት እንዲወድም ምክንያት ሆነዋል የተባሉ ካድሬዎች ተገድለዋል ብሏል፡፡
ሰሜን ኮሪያ በፓሪስ ኦሎምፒክ ከደቡብ ኮሪያ አትሌቶች ጋር ፎቶ የተነሱ ስፖርተኞቿን ልትቀጣ ነው
ዘገባው አክሎም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን በጎርፍ የተጥለቀለቁ አካባቢዎችን ከጎበኙ በኋላ ከ20 -30 የሚደርሱ ካድሬዎች እንዲገደሉ ውሳኔ አሳልፈዋል ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ኪም መኖሪያ ቤታቸው በጎርፍ የተወሰደባቸው ዜጎች አካባቢዎችን በአካል ተገኝተው ከጎበኙ በኋላ በወቅቱ አዝነዋል ተብሎም ነበር፡፡
በሐምሌ ወር ሰሜን ኮሪያን ጨምሮ ቻይና እና ሌሎችም የእስያ ሀገራት በጎርፍ አደጋ ክፉኛ መመታታቸው አይዘነጋም፡፡