የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ባለስልጣን ጦሩ ሰሜን ኮሪያዊው ወታደር ለምን አላማ እንዳቋረጠ እያጣራ ነው ብለዋል
የሰሜን ኮሪያ ወታደር ወደ ደቡብ ኮሪያ መክዳቱ ተገለጸ።
የሰሜን ኮሪያ ወታደር ከፍታኛ ወታደራዊ ጥበቃ በሚደረግበት በምስራቃዊ የኮሪያ ባህረ ሰላጤ በኩል በዛሬው እለት ወደ ደቡብ ኮሪያ መክዳቱን ሮይተርስ ዩንሀፕ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ዘግቧል።
ወታደሩ ሰሜን ኮሪያን በምስራቅ በኩሉ ወደምታዋስነው ጎዝኦንግ ግዛት አቋርጦ የገባ ሲሆን እንቅስቃሴውን ሲከታተሉ በነበሩት የደቡብ ኮሪያ የድንበር ጠባቂዎች መያዙን ዘገባው ጠቅሷል።
የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ባለስልጣን ጦሩ ሰሜን ኮሪያዊ ነው ተብሎ የሚታመነውን ሰው በምስራቅ ግንባር በቁጥጥር ስር ማዋሉን እና ለምን አላማ እንዳቋረጠ እያጣራ ነው ብለዋል።
እንዘገባው ከሆነ ይህ የሰሜን ኮሪያ ወታደር ወሰረታዊ የቢሮ ጥበቃ የነበረ ነው።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ደቡብ ኮሪያዊ ነዋሪ በምዕራብ በኩል ወደ ደቡብ ኮሪያ ከድተዋል።
በኩባ የነበሩ ሪ ኢል ኪዩ የተባሉ ከፍተኛ የሰሜን ኮሪያ ዲፕሎማት ባለፈው ሀምሌ ወር ወደ ደቡብ ኮሪያ መክዳታቸውን የደበብ ኮሪያ ደህንነት ይታወሳል። ዲፕሎማቱ ከፈረንጆቹ 2016 ወዲህ ወደ ደቡብ ኮሪያ የከዱ ከፍተኛ ባለስልጣን መሆናቸውም ተዘግቧል።
ሰሜን ኮሪያውያን ወደ ደቡብ ኮሪያ የሚያደርጉት መኮብለል እጅግ አደገኛ እና አልፎ አልፎ የሚደረግ ሲሆን አብዛኞቹ ያመለጡት ሰዎች በቻይና ወይም በሌላ ሶስተኛ ሀገር አድርገው ወደ ደቡብ ኮሪያ ይገባሉ።