ብሊንከን ሴኡልን እየጎበኙ ባለበት ወቅት ሰሜን ኮሪያ የመካከለኛው ርቀት ሚሳይል አስወነጨፈች
የደቡብ ኮሪያ ጦር እንደገለጸው ሰሜን ኮሪያ ባህር ውስጥ ከማረፉ በፊት 1000 ኪሎሜትር የተምዘገዘገ የመካከለኛው ርቀት የሚመስል ሚሳይል አስወንጭፋለች
ብሊንከን የሚሳይል ሙከራው የአሜሪካ፣ ሴኡል እና ደቡብ ኮሪያን ትብብር አስፈላጊነት ትኩረት እንዲሰጠው ያደርጋል ብለዋል
ብሊንከን ሴኡልን እየጎበኙ ባለበት ወቅት ሰሜን ኮሪያ የመካከለኛው ርቀት ሚሳይል አስወነጨፈች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰሜን ኮሪያ በሴኡል ጉብኝት እያካሄዱ ባለበት ወቅት የሚሳይል ሙከራ ማድረጓ ዋሽንግተን ፒዮንግያንግ ለመመከት ከደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ጋር ያላትን ግንኙነት መጠናከር እንዳለባት የሚያሳይ ሲሉ በዛሬው እለት ተናግረዋል።
የደቡብ ኮሪያ ጦር እንደገለጸው ሰሜን ኮሪያ ባህር ውስጥ ከማረፉ በፊት 1000 ኪሎሜትር የተምዘገዘገ የመካከለኛው ርቀት የሚመስል ሚሳይል አስወንጭፋለች።
ብሊንከን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በሰጡት መግለጫ የሚሳይል ሙከራው የአሜሪካ፣ ሴኡል እና ደቡብ ኮሪያን ትብብር አስፈላጊነት ትኩረት እንዲሰጠው ያደርጋል ብለዋል።
"የዛሬው ሙከራ ትብብራችን ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳይ ነው" ብለዋል ብሊንከን።
ብሊንከን ከሞስኮ ጋር ወታደራዊ ግንኙነቷን እያጠናከረች የምትገኘውን ሰሜን ኮሪያን አስጠንቅቀዋል። ብሊንከን አክለውም እንደገለጹት ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ከሞስኮ ጎን ተሰልፈው በሚዋጉት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ምትክ ሩሲያ የስፔስ እና የሳተላይት ቴክኖሎጂ ለሰሜን ኮሪያ ታጋራለች ብለው ያምናሉ።
በዚህ ወር ከኃይት ሀውስ የሚወጡት ፕሬዝደንት ባይደን በአሜሪካ፣ በደቡብ ኮሪያ ኤና ጃፓን መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር ጥረት ማድረጋቸው ይገለጻል።
ነገርግን በደቡብ ኮሪያ ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ከማይተነበዩት ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ትራምፕ ወደ ኃይት ሀውስ መመለስ ጋር ተዳምሮ እነዚህ ጥረቶች መቀጠል መቻላቸውን ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል።
የደቡብ ኮሪያ ፓርላማ ባለፈው ወር በሀገሪቱ ለአጭር ጊዜ የቆየውን ወታደራዊ ህግ ያወጁትን ፕሬዝደንት ዩን ከስልጣን አግዷል። የዩን ጉዳይ በአሁኑ ወቅት በህገመንግስታዊ ፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።
ዩን በቋሚነት ከስልጠን የሚነሱ ከሆነ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እንደሚካሄድ እና ሴኡል ከቶኪዮ ጋር ያላትን ግንኙነት የሚተቹ ሊበራሎች የማሸነፍ እድላቸው የሰፋ ነው ተብሏል።
ጊዜያዊ ፕሬዝደንቱን ቾይ ሳንግ ሞክን ያገኙት ብሊንከን ዋሽንግተን በዩን ድርጊት ከባድ ስጋት ቢኖራትም በሀገሪቱ ተቋማት እና ዲሞክራሲ ቁርጠኝነት እንደሚተማኑ ገልጸዋል።
ዩን ግጭት በመቀስቀስ ተጠርጥረው እንዲታሰሩ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የመያዣ ትዕዛዝ ቢያጸድቅም፣ በጸጥታ አካላት መካከል በተፈጠረው ፍጥጫ ምክንያት ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል።
የአሁኑ የፒዮግያንግ ሙከራ ባለፈው ሐምሌ 5፣2024 ሰባት የአጭር ርቀት ሚሳይሎች ከሞከረች ወዲህ የመጀመሪያ ነው። የተወነጨፈው ሚሳይል ምን አይነት እንደሆነ በትክክል ባይታወቅም፣ ባለፈው አመት ሰሜን ኮሪያ ጥጥር ነዳጅ የሚጠቀም ሚሳይል ማስወንጨፏን መግለጿ ይታወሳል።