አሜሪካ የሰሜን ኮሪያ ሚሳይል ጥቃት የኪም አስተዳዳር ማብቃያ ይሆናል ስትል አስጠነቀቀች
የደቡብ ኮሪያ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳይል በዚህ ወር ሳትሞክር እንዳልቀረች ተናግረዋል
ሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፖን እና አሜሪካ ሊደርሱ የሚችሉ በርካታ የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ሰርታ ሞክራለች
አሜሪካ የሰሜን ኮሪያ ሚሳይል ጥቃት የኪም አስተዳዳር ማብቃያ ይሆናል ስትል አስጠነቀቀች።
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ እና በአጋሮቿ ላይ የምትሰነዝረው ማንኛውም የሚሳይል ጥቃት ተቀባይት የሌለው እና የኪም ጆንግ ኡን አስተደዳር ማብቂያ እንደሚሆን ማስጠንቀቋን አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ያወጡት የጋራ መግለጫ ጠቅሷል።
መግለጫው "በአሜሪካ በኩል ሰሜን ኮሪያ በደቡብ ኮሪያ ላይ ልታደርግ የምትችለው ማንኛውም ጥቃት ፈጣን እና የማያዳግም ምላሽ ይሰጠዋል" ብሏል።
ሁለተኛው የአሜሪካ-ደቡብ ኮሪያ ኑክሌር ኮንሰልታቲቭ ቡድን (ኤንሲሲ) ስብሰባ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ሰሜን ኮሪያ ወደ ግጭት ቢገቡ የኑክሌር ጥቃት ለመመከት ምን መደረግ አለበት በሚለው ጉዳይ መክሯል። ሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፖን እና አሜሪካ ሊደርሱ የሚችሉ በርካታ የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ሰርታ ሞክራለች።
የደቡብ ኮሪያ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳይል በዚህ ወር ሳትሞክር እንዳልቀረች ተናግረዋል።
ሶስተኛው የአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ኤንሲሲ በሚቀጥለው ክረምት በደቡብ ኮሪያ ይካሄዳል።
የአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ የሚያደርጉትን ወታደራዊ ልምምድ የምትቃወመው ሰሜን ኮሪያ ራሷን ለመከላከል ወታደራዊ ዝግጅቷን እንደምትቀጥል በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወሳል።